YouVersion Logo
Search Icon

ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 7

7
ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕት ሕግ
1“የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው። 2የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ር​ዱ​በት ስፍራ የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕት በግ በዚያ ያር​ዱ​ታል፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ይረ​ጩ​ታል። 3ስቡ​ንም ሁሉ፥ ላቱ​ንም፥ የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ ሁሉ፥ በአ​ን​ጀ​ቱም ላይ ያለ​ውን ስብ፤ 4ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በእ​ነ​ር​ሱም ላይና በጎ​ድኑ አጠ​ገብ ያለ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ ከኵ​ላ​ሊ​ቶቹ ጋር ካህኑ ይለ​ያል። 5ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ እር​ሱም የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ነው። 6ከካ​ህ​ናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበ​ላ​ዋል፤ በተ​ቀ​ደሰ ስፍ​ራም ይበ​ሉ​ታል፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው። 7የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት እንደ ሆነ እን​ዲሁ የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ነው፤ ለሁ​ለቱ አንድ ሕግ ነው፤ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ተ​ሰ​ርይ ካህን ይወ​ስ​ደ​ዋል። 8የሰ​ውን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ ካህን ያቀ​ረ​በው የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ቍር​በት ለዚ​ያው ካህን ይሆ​ናል። 9በእ​ቶን የተ​ጋ​ገ​ረው የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ፥ በመ​ቀ​ቀ​ያም ወይም በም​ጣድ የበ​ሰ​ለው ሁሉ ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ካህን ይሆ​ናል።#ምዕ. 7 ቍ. 9 በግ​እዙ የለም። 10በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወ​ሰው ወይም የደ​ረ​ቀው የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ ለአ​ሮን ልጆች ሁሉ ይሆ​ናል፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም እኩል ይሆ​ናል።
ስለ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ
11“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው። 12ለም​ስ​ጋና ቢያ​ቀ​ር​በው፥ ከም​ስ​ጋ​ናው መሥ​ዋ​ዕት ጋር በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የቂጣ እን​ጎቻ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ያቀ​ር​ባል። 13ለም​ስ​ጋና የሚ​ሆ​ነ​ውን የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት በአ​ቀ​ረበ ጊዜ እርሾ ያለ​በ​ትን ኅብ​ስት ያቀ​ር​ባል። 14ከቍ​ር​ባ​ኑም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድርሻ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ያነ​ሣል። እር​ሱም የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ደም ለሚ​ረ​ጨው ካህን ይሆ​ናል።
15“ለም​ስ​ጋና የሚ​ሆ​ነው የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋም ለእ​ርሱ ነው፤ በሚ​ቀ​ር​ብ​በ​ትም ቀን ይበ​ሉ​ታል፤ ከእ​ርሱ እስከ ነገ ምንም አያ​ተ​ር​ፉም። 16የቍ​ር​ባ​ኑም መሥ​ዋ​ዕት የስ​እ​ለት ወይም የፈ​ቃድ ቢሆን፥ መሥ​ዋ​ዕቱ በሚ​ቀ​ር​ብ​በት ቀን ይብ​ሉት፤ ከእ​ር​ሱም የቀ​ረ​ውን በነ​ጋው ይብ​ሉት፤ 17ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም ሥጋ እስከ ሦስ​ተ​ኛው ቀን የሚ​ቈ​የ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል። 18በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይ​ሠ​ም​ርም፤ ላቀ​ረ​በው ሰው የተ​ጠላ ይሆ​ን​በ​ታል እንጂ ቍር​ባን ሆኖ አይ​ቈ​ጠ​ር​ለ​ትም፤ ከእ​ር​ሱም የበላ ሰው ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።
19“ርኩስ ነገር የሚ​ነ​ካ​ውን ሥጋ አይ​ብ​ሉት፤ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉት እንጂ። ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ግን ከሥ​ጋው ይብላ። 20ኀጢ​አት ሳለ​ባት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ የበ​ላች ሰው​ነት፥ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ። 21ከር​ኩስ ሁሉ፥ ወይም ከረ​ከ​ሰው ሰው፥ ወይም ንጹሕ ካል​ሆ​ነው እን​ስሳ የነ​ካች ሰው​ነት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ብት​በላ፥ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።”
ስብ​ንና ደምን መብ​ላት ስለ​ማ​ይ​ገባ
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 23“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍ​የል ስብ ከቶ አት​ብሉ። 24የሞ​ተ​ውን ስብ፥ አውሬ የሰ​በ​ረ​ው​ንም ስብ ለሌላ ተግ​ባር አድ​ር​ጉት፤ እና​ንተ ግን አት​ብ​ሉት፤ 25ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳት ከሚ​ቀ​ር​በው ከእ​ን​ስሳ ስብ የሚ​በላ ሁሉ ያች የበ​ላች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ። 26በመ​ኖ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ሁሉ የወፍ ወይም የእ​ን​ስሳ ደም ቢሆን አት​ብሉ። 27ደም የም​ት​በላ ሰው​ነት ሁሉ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።”
ከደ​ኅ​ን​ነ​ቱና ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት የካ​ህ​ናት ዕድል ፈንታ
28እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 29“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ ሰው ቍር​ባ​ኑን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከደ​ኅ​ን​ነቱ መሥ​ዋ​ዕት ያመ​ጣል። 30የእ​ርሱ እጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳ​ቱን ቍር​ባን ያመ​ጣሉ፤ ፍር​ም​ባ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቍር​ባን ያቀ​ርብ ዘንድ በጉ​በቱ ላይ ያለ​ውን መረ​ብና የፍ​ር​ም​ባ​ውን ስብ ያመ​ጣል። 31ካህ​ኑም ስቡን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረው፤ ፍር​ም​ባ​ውም ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሁን። 32ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ቀኝ ወር​ቹን ለማ​ን​ሣት ቍር​ባን እን​ዲ​ሆን ለካ​ህኑ ትሰ​ጡ​ታ​ላ​ቸሁ። 33ከአ​ሮ​ንም ልጆች የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ደሙ​ንና ስቡን ለሚ​ያ​ቀ​ርብ ለእ​ርሱ ቀኝ ወርቹ እድል ፈን​ታው ይሆ​ናል። 34ፍር​ም​ባ​ው​ንና የቀኝ ወር​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ ለካ​ህኑ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ።”
35እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ በተ​ቀ​ቡ​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆነ ከእ​ሳት ቍር​ባን የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ ሕግ ይህ ነው። 36ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን በቀ​ባ​ቸው ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ይህ ነው። 37የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህል ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ትና የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት፥ የቅ​ድ​ስ​ናና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው። 38እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ምድረ በዳ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ርቡ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘ​ዘው ይህ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in