YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ዮናስ 4

4
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረ​ትና የዮ​ናስ ብስ​ጭት
1ዮና​ስም ፈጽሞ አዘነ፤ ተከ​ዘም። 2ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ በሀ​ገሬ ሳለሁ የተ​ና​ገ​ር​ሁት ይህ አል​ነ​በ​ረ​ምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋ​ሽም፥ ምሕ​ረ​ት​ህም የበዛ፥ ከክ​ፉው ነገ​ርም የም​ት​መ​ለስ አም​ላክ እንደ ሆንህ ዐውቄ ነበ​ርና ስለ​ዚህ ወደ ተር​ሴስ ለመ​ኰ​ብ​ለል ፈጥኜ ነበር። 3አሁ​ንም አቤቱ! ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛ​ልና እባ​ክህ! ነፍ​ሴን ከእኔ ውሰድ።” 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን፥ “ፈጽ​መህ ታዝ​ና​ለ​ህን?” አለው።
5ዮና​ስም ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጣ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ለፊት#ዕብ. “በስተ ምሥ​ራቅ በኩል” ይላል። ተቀ​መጠ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም የሚ​ሆ​ነ​ውን እስ​ኪ​ያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥ​ላው በታች ተቀ​መጠ። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ቅልን አዘዘ፤ ከጭ​ን​ቀ​ቱም ታድ​ነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እን​ድ​ት​ሆን በዮ​ናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ጋት፤ ዮና​ስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው። 7በነ​ጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትልን አዘዘ፤ እር​ስ​ዋም ቅሊ​ቱን መታ​ቻት፤ ደረ​ቀ​ችም። 8ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትኩስ የም​ሥ​ራቅ ነፋ​ስን አዘዘ፤ ዮና​ስ​ንም እስ​ኪ​ዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራ​ሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕ​ይ​ወት ሞት ይሻ​ለ​ኛል” አለ። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን፥ “በውኑ ስለ​ዚች ቅል ታዝ​ና​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እስ​ክ​ሞት ድረስ እጅግ አዝ​ኛ​ለሁ” አለ። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አንተ ትበ​ቅል ዘንድ ላል​ደ​ከ​ም​ህ​ባት፥ ላላ​ሳ​ደ​ግ​ሃ​ትም፥ በአ​ንድ ሌሊት ለበ​ቀ​ለች፥ በአ​ንድ ሌሊ​ትም ለደ​ረ​ቀ​ችው ቅል አዝ​ነ​ሃል። 11እኔስ ቀኛ​ቸ​ው​ንና ግራ​ቸ​ውን የማ​ይ​ለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚ​በ​ልጡ ሰዎ​ችና ብዙ እን​ስ​ሶች ላሉ​ባት ለታ​ላ​ቂቱ ከተማ ለነ​ነዌ አላ​ዝ​ን​ምን?” አለው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in