YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ኢዩ​ኤል 2

2
አን​በጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መም​ጣት እን​ደ​ሚ​ያ​መ​ለ​ክት
1በጽ​ዮን መለ​ከ​ትን ንፉ፤ በቅ​ዱ​ሱም ተራ​ራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይደ​ን​ግጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን መጥ​ቶ​አ​ልና፥ እር​ሱም ቀር​ቦ​አ​ልና። 2የጨ​ለ​ማና የነ​ፋስ ቀን፥ የደ​መ​ናና የጉም ቀን ነው፤ ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ወገ​ግታ ተዘ​ር​ግ​ቶ​አል፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይ​ሆ​ንም። 3እሳት በፊ​ታ​ቸው ትበ​ላ​ለች፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ል​ባል ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ሪቱ በፊ​ታ​ቸው እንደ ደስታ ገነት፥ በኋ​ላ​ቸ​ውም እንደ ምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእ​ር​ሱም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።
4መል​ካ​ቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፤ እንደ ፈረ​ሶ​ችም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ ፈረ​ሰ​ኞች” ይላል። ይሮ​ጣሉ። 5ድም​ፃ​ቸ​ውም በተ​ራራ ላይ እንደ አሉ ሠረ​ገ​ሎች ድምፅ፥ ገለ​ባ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​በላ እንደ እሳት ነበ​ል​ባል ድምፅ ነው፤ ለሰ​ል​ፍም እንደ ተዘ​ጋጀ እንደ ብዙና ብርቱ ሠራ​ዊት ያኰ​በ​ኵ​ባሉ። 6ከፊ​ታ​ቸው አሕ​ዛብ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ የሰ​ውም ፊት ሁሉ እንደ ድስት ጥላ​ሸት ይጠ​ቍ​ራል። 7እንደ ተዋ​ጊ​ዎች ይሮ​ጣሉ፤ እንደ ጦረ​ኞ​ችም በቅ​ጥሩ ላይ ይወ​ጣሉ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በመ​ን​ገዱ ላይ ይራ​መ​ዳል፤ ከእ​ር​ም​ጃ​ቸ​ውም አያ​ፈ​ገ​ፍ​ጉም። 8አንዱ ከሌ​ላው ርቆ አይ​ቆ​ምም፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ይሮ​ጣሉ፤ በመ​ሣ​ሪ​ያ​ቸው ላይ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እነ​ር​ሱም አይ​ጠ​ፉም። 9ከተ​ሞ​ችን ይይ​ዛሉ፤ በቅ​ጥ​ሩም ላይ ይሮ​ጣሉ፤ ወደ ቤቶ​ችም ይወ​ጣሉ፤ እንደ ሌባም በመ​ስ​ኮ​ቶች ይገ​ባሉ። 10ምድ​ሪ​ቱም ከፊ​ታ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ሰማ​ይም ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣል፤ ፀሐ​ይና ጨረ​ቃም ይጨ​ል​ማሉ፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን ይሰ​ው​ራሉ። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሠ​ራ​ዊቱ ፊት ድም​ፁን ይሰ​ጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ የቃ​ሉም ሥራ ጽኑዕ ነውና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀን ታላ​ቅና እጅግ የም​ታ​ስ​ፈራ ናትና፥ ፈጽማ ትገ​ለ​ጣ​ለች፥ መጠኗ ምን​ድን ነው? ማንስ ይች​ላ​ታል?
12አሁ​ንስ ይላል አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “በፍ​ጹም ልባ​ችሁ በጾም፥ በል​ቅ​ሶና በዋ​ይታ ወደ እኔ ተመ​ለሱ። 13ልባ​ች​ሁን እንጂ ልብ​ሳ​ች​ሁን አት​ቅ​ደዱ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ፥ ቍጣው የዘ​ገየ ምሕ​ረ​ቱም የበዛ፥ ለክ​ፋ​ትም የተ​ጸ​ጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመ​ለሱ።” 14የሚ​መ​ለ​ስና የሚ​ጸ​ጸት እንደ ሆነ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን የሚ​ሆን በረ​ከ​ትን በኋላ የሚ​ያ​ተ​ርፍ እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?
15በጽ​ዮን መለ​ከ​ትን ንፉ፤ ጾም​ንም ቀድሱ፤ ምህ​ላ​ንም ዐውጁ፤ 16ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቡ፤ ማኅ​በ​ሩ​ንም ቀድሱ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹ​ንም ጥሩ፤ ጡት የሚ​ጠ​ቡ​ት​ንና ሕፃ​ና​ትን ሰብ​ስቡ፤ ሙሽ​ራው ከእ​ል​ፍኙ፥ ሙሽ​ራ​ዪ​ቱም ከጫ​ጕ​ላዋ ይውጡ። 17የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች ካህ​ናት በወ​ለ​ሉና በም​ሥ​ዋዑ መካ​ከል እያ​ለ​ቀሱ፥ “አቤቱ! ለሕ​ዝ​ብህ ራራ፤ አሕ​ዛ​ብም ይገ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ርስ​ት​ህን ለማ​ላ​ገጫ አሳ​ል​ፈህ አት​ስጥ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል፦ አም​ላ​ካ​ቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ?” ይበሉ።
18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ምድሩ ቀና፤ ለሕ​ዝ​ቡም ራራ​ለት። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መልሶ ሕዝ​ቡን፥ “እነሆ እህ​ል​ንና ወይ​ንን፥ ዘይ​ት​ንም እሰ​ድ​ድ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በእ​ርሱ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲያ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል መሰ​ደ​ቢያ አላ​ደ​ር​ጋ​ች​ሁም። 20የሰ​ሜ​ን​ንም ሠራ​ዊት ከእ​ና​ንተ ዘንድ አር​ቃ​ለሁ፤ ወደ በረ​ሃና ወደ ምድረ በዳ እሰ​ደ​ዋ​ለሁ፤ ፊቱን ወደ መጀ​መ​ሪ​ያው#ዕብ. “ምሥ​ራቁ” ይላል። ባሕር፥ ጀር​ባ​ው​ንም ወደ ኋለ​ኛው#ዕብ. “ምዕ​ራብ” ይላል። ባሕር አድ​ርጌ አሳ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ትዕ​ቢ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ግማቱ ይወ​ጣል፤ ክር​ፋ​ቱም ይነ​ሣል።”
21“ምድር ሆይ! አት​ፍሪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነገር አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ። 22እና​ንተ የም​ድር እን​ስ​ሶች ሆይ! የም​ድረ በዳው ማሰ​ማ​ርያ ለም​ል​ሞ​አ​ልና፥ ዛፉም ፍሬ​ውን አፍ​ር​ቶ​አ​ልና፥ በለ​ሱና ወይ​ኑም ኀይ​ላ​ቸ​ውን ሰጥ​ተ​ዋ​ልና አት​ፍሩ። 23እና​ንተ የጽ​ዮን ልጆች ሆይ! በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጉ፤ ምግ​ብን በጽ​ድቅ ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ቀድ​ሞ​ውም የበ​ል​ጉ​ንና የመ​ከ​ሩን ዝናብ ያዘ​ን​ብ​ላ​ች​ኋ​ልና። 24ዐው​ድ​ማ​ዎ​ችም እህ​ልን ይሞ​ላሉ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ዎ​ችም የወ​ይን ጠጅ​ንና ዘይ​ትን አት​ረ​ፍ​ር​ፈው ያፈ​ስ​ሳሉ። 25የሰ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ችሁ ታላቁ ሠራ​ዊቴ አን​በ​ጣና ደጎ​ብያ፥ ኩብ​ኩ​ባና ተምች ስለ በላ​ቸው ዓመ​ታት እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ። 26ብዙ መብል ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ትጠ​ግ​ቡ​ማ​ላ​ችሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ተአ​ም​ራ​ትን የሠ​ራ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ታመ​ሰ​ግ​ና​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ቤም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም። 27እኔም በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል እን​ዳ​ለሁ፥ እኔም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ቤም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም።
28“ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ መን​ፈ​ሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም ትን​ቢ​ትን ይና​ገ​ራሉ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ች​ሁም ራእ​ይን ያያሉ፤ 29ደግ​ሞም በዚያ ወራት በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች ባሪ​ያ​ዎች ላይ መን​ፈ​ሴን አፈ​ስ​ሳ​ለሁ። 30በላይ በሰ​ማይ ድን​ቆ​ችን አሳ​ያ​ለሁ፤ በታች በም​ድ​ርም ደምና እሳት የጢ​ስም ጭጋግ። 31ታላ​ቋና ግልጥ የሆ​ነ​ችው#ዕብ. “የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራው” ይላል። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ሳት​መጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረ​ቃም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል። 32እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ ሁሉ ይድ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይድ​ናሉ። ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጠ​ራ​ቸው፥ የም​ሥ​ራች የሚ​ሰ​በ​ክ​ላ​ቸው ይገ​ኛሉ።#ምዕ. 2 ከቍ. 28 እስከ 32 ያለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 3 ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in