መጽሐፈ ኢዮብ 26
26
የኢዮብ መልስ
1ኢዮብም መለሰ፥ እንዲህም አለ፦
2“ማንን ትደግፋለህ? ማንንስ ልትረዳ ትወድዳለህ?
ጥንቱን ኀይሉ ብዙ፥ ክንዱም ጽኑ የሆነ እርሱ አይደለምን?
3ለማንስ ታማክራለህ?
ጥበብ ሁሉ ለእርሱ አይደለምን?
ማንንስ ትከተላለህ? ታላቅ ኀይል ያለው እርሱ አይደለምን?#በዕብራይስጥ ልዩነት አለ።
4ነገርን ለማን ትናገራለህ?
የማንስ መንፈስ ከአንተ ዘንድ ይወጣል?
5ኀያላን ከውኆች በታች፥
በውኆችም ውስጥ ከሚኖሩ ይወለዳሉን?
6ሲኦል በፊቱ ራቁቱን ነው፥
ሞትንም ከእርሱ የሚጋርደው የለም።
7ሰማይን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል፥
ምድሪቱንም አንዳች አልባ ያንጠለጥላል።
8ውኃውን በደመና ውስጥ ይቋጥራል፥
ደመናውም ከታች አይቀደድም።
9የዙፋኑን ፊት ይከድናል፥
ደመናውንም ይዘረጋበታል።
10ብርሃን ከጨለማ እስከሚለይበት ዳርቻ ድረስ፥
የውኃውን ፊት በተወሰነ ትእዛዙ ከበበው።
11የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ፥
ከተግሣጹም የተነሣ ይደነግጣሉ።
12በኀይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፥
በማስተዋሉም ዐንበሪውን ይገለብጠዋል።
13የሲኦል#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሰማይ” ይላል። በረኞች ለእርሱ አደሉ።#ዕብ. “በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ” ይላል።
በትእዛዙም ዐመፀኛውን እባብ ገደለው።
14እነሆ ይህ የመንገዱ ክፍል ነው፤
የቀሩትንም ነገሮቹን እንሰማለን፤
በሚያደርግበትስ ጊዜ የነጐድጓዱን ኀይል የሚያውቅ ማን ነው?”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 26: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in