YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 26

26
የኢ​ዮብ መልስ
1ኢዮ​ብም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦
2“ማንን ትደ​ግ​ፋ​ለህ? ማን​ንስ ልት​ረዳ ትወ​ድ​ዳ​ለህ?
ጥን​ቱን ኀይሉ ብዙ፥ ክን​ዱም ጽኑ የሆነ እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?
3ለማ​ንስ ታማ​ክ​ራ​ለህ?
ጥበብ ሁሉ ለእ​ርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?
ማን​ንስ ትከ​ተ​ላ​ለህ? ታላቅ ኀይል ያለው እርሱ አይ​ደ​ለ​ምን?#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ልዩ​ነት አለ።
4ነገ​ርን ለማን ትና​ገ​ራ​ለህ?
የማ​ንስ መን​ፈስ ከአ​ንተ ዘንድ ይወ​ጣል?
5ኀያ​ላን ከው​ኆች በታች፥
በው​ኆ​ችም ውስጥ ከሚ​ኖሩ ይወ​ለ​ዳ​ሉን?
6ሲኦል በፊቱ ራቁ​ቱን ነው፥
ሞት​ንም ከእ​ርሱ የሚ​ጋ​ር​ደው የለም።
7ሰማ​ይን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘ​ረ​ጋል፥
ምድ​ሪ​ቱ​ንም አን​ዳች አልባ ያን​ጠ​ለ​ጥ​ላል።
8ውኃ​ውን በደ​መና ውስጥ ይቋ​ጥ​ራል፥
ደመ​ና​ውም ከታች አይ​ቀ​ደ​ድም።
9የዙ​ፋ​ኑን ፊት ይከ​ድ​ናል፥
ደመ​ና​ው​ንም ይዘ​ረ​ጋ​በ​ታል።
10ብር​ሃን ከጨ​ለማ እስ​ከ​ሚ​ለ​ይ​በት ዳርቻ ድረስ፥
የው​ኃ​ውን ፊት በተ​ወ​ሰነ ትእ​ዛዙ ከበ​በው።
11የሰ​ማይ አዕ​ማድ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፥
ከተ​ግ​ሣ​ጹም የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።
12በኀ​ይሉ ባሕ​ርን ጸጥ ያደ​ር​ጋል፥
በማ​ስ​ተ​ዋ​ሉም ዐን​በ​ሪ​ውን ይገ​ለ​ብ​ጠ​ዋል።
13የሲ​ኦል#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሰ​ማይ” ይላል። በረ​ኞች ለእ​ርሱ አደሉ።#ዕብ. “በመ​ን​ፈሱ ሰማ​ያት ውበ​ትን አገኙ” ይላል።
በት​እ​ዛ​ዙም ዐመ​ፀ​ኛ​ውን እባብ ገደ​ለው።
14እነሆ ይህ የመ​ን​ገዱ ክፍል ነው፤
የቀ​ሩ​ት​ንም ነገ​ሮ​ቹን እን​ሰ​ማ​ለን፤
በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በ​ትስ ጊዜ የነ​ጐ​ድ​ጓ​ዱን ኀይል የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው?”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መጽ​ሐፈ ኢዮብ 26