YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 24

24
1“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመ​ኖ​ችን ለምን ረሳ​ቸው?#ዕብ​ራ​ይ​ስጥ ተጨ​ማሪ አለው።
2ኃጥ​ኣን የድ​ን​በ​ሩን ምል​ክት አለፉ፤
እረ​ኛ​ው​ንም ከመ​ን​ጋ​ዎቹ ጋር ይነ​ጥ​ቃሉ።
3የድ​ሃ​አ​ደ​ጎ​ቹን አህያ ይነ​ዳሉ
የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም በሬ ስለ መያዣ ይወ​ስ​ዳሉ።
4ደካ​ሞ​ችን ከእ​ው​ነት መን​ገድ ያወ​ጣሉ፤
የም​ድ​ርም የዋ​ሃን ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ይሸ​ሸ​ጋሉ።
5እነሆ፥ በም​ድረ በዳ እን​ዳሉ እንደ ሜዳ አህ​ዮች ሆኑ።
ስለ እኔም ሥራ​ቸ​ውን ትተው ይወ​ጣሉ፤
መብል፦ ከል​ጅ​ነ​ታ​ቸው ጀምሮ ይጥ​ማ​ቸ​ዋል።
6“የራ​ሳ​ቸው ያል​ሆ​ነ​ውን እርሻ ያለ ሰዓቱ ያጭ​ዳሉ።
ኃጥ​ኣን ድሆ​ችን በወ​ይ​ና​ቸው ቦታ ያለ ዋጋና ያለ ቀለብ ያሠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።
7ብዙ​ዎ​ችን የተ​ራ​ቈ​ቱ​ት​ንም ያለ ልብስ ያሳ​ድ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።
መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ቸ​ው​ንም ይገ​ፍ​ፏ​ቸ​ዋል።
8በካ​ፊ​ያና ከተ​ራ​ሮች በሚ​ወ​ርድ ጠል ይረ​ጥ​ባሉ፤
መጠ​ጊ​ያም የላ​ቸ​ው​ምና ቋጥ​ኙን ተተ​ገኑ።
9ድሃ​አ​ደ​ጉን ልጅ ከጡቱ ይነ​ጥ​ላሉ፤
ችግ​ረ​ኛ​ው​ንም ያሠ​ቃ​ያሉ።
10ችግ​ረ​ኞ​ችን በደ​ሉ​አ​ቸው፥ ጣሉ​አ​ቸ​ውም፤
ከተ​ራ​ቡ​ትም የሚ​ጐ​ር​ሱ​ትን ነጠ​ቋ​ቸው።
11በጠ​ባብ ቦታ በዐ​መፅ ይሸ​ም​ቃሉ፥#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ታላቅ ልዩ​ነት አለው።
የጽ​ድ​ቅ​ንም መን​ገድ አያ​ው​ቁም።
12ድሆ​ችን ከከ​ተ​ማ​ውና ከገዛ ቤቶ​ቻ​ቸው አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው
የሕ​ፃ​ና​ት​ንም ነፍስ እጅግ አስ​ጮሁ፤
13“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እነ​ዚ​ህን ለምን አል​ገ​ሠ​ጻ​ቸ​ውም?
በም​ድር ላይ ሳሉ አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም፥
የቅ​ን​ነት መን​ገ​ድ​ንም አላ​ዩም።
በአ​ደ​ባ​ባ​ይ​ዋም አል​ሄ​ዱም።
14ሥራ​ቸ​ው​ንም ዐውቆ ለጨ​ለማ ዳረ​ጋ​ቸው።
በሌ​ሊ​ትም እንደ ሌባ ናቸው።
15የአ​መ​ን​ዝ​ራም ዐይን ድግ​ዝ​ግ​ዝ​ታን ይጠ​ብ​ቃል፦
የማ​ንም ዐይን አያ​የ​ኝም ይላል፥
ፊቱ​ንም ይሸ​ፍ​ናል።
16በጨ​ለማ ቤቶ​ችን ይነ​ድ​ላል፤
በቀን ይሸ​ሸ​ጋሉ፤ ብር​ሃ​ን​ንም አያ​ዩም።
17የጥ​ዋት ብር​ሃን ለእ​ነ​ርሱ ሁሉ እንደ ሞት ጥላ ነው፤
የሚ​ሆ​ነ​ውን ድን​ጋጤ ያው​ቃ​ሉና።
ሞት​ንም ይጠ​ራ​ጠ​ራ​ሉና።
18እርሱ በውኃ ፊት ላይ በርሮ ያል​ፋል፤
እድል ፋን​ታ​ውም በም​ድር ላይ የተ​ረ​ገ​መች ናት፤
19ተክ​ላ​ቸው በም​ድር ላይ ሲደ​ርቅ ያያሉ።
ያላ​ቸ​ውም ድሀ​ኣ​ደ​ጉን በዘ​በ​ዙት።
20ከዚ​ህም በኋላ ኀጢ​አ​ቱን ያስ​ባል።
እንደ ጤዛ ትነት ይጠ​ፋል።
እንደ ሥራ​ውም ይከ​ፈ​ለ​ዋል።
ዐመ​ፀ​ኛም ሁሉ እንደ በሰ​በሰ ዛፍ ይሰ​በ​ራል።
21ለማ​ት​ወ​ል​ደው ለመ​ካ​ኒቱ በጎ​ነ​ትን አላ​ደ​ረ​ገ​ላ​ትም፤
ለም​ት​ወ​ል​ደ​ውም#ግሪኩ “ለደ​ካ​ማ​ይቱ” ይላል። አል​ራ​ራም።
22ነገር ግን ረዳት የሌ​ላ​ቸ​ውን በቍ​ጣው አጠ​ፋ​ቸው።
እር​ሱም በተ​ነሣ ጊዜ ሰው በሕ​ይ​ወቱ አይ​ታ​መ​ንም።
23በታ​መ​መም ጊዜ መዳ​ንን ተስፋ አያ​ደ​ር​ግም።
ነገር ግን እርሱ በሕ​ማሙ ይሞ​ታል።
24ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙ​ዎ​ችን አስ​ጨ​ነ​ቃ​ቸው።
እንደ አመ​ድ​ማዶ በሙ​ቀት ይጠ​ወ​ል​ጋል።
ከቃ​ር​ሚ​ያው እን​ደ​ሚ​ወ​ድቅ እሸ​ትም ይቈ​ረ​ጣል።
25እን​ዲ​ህስ ባይ​ሆን ሐሰ​ተኛ ነህ የሚ​ለኝ፥
ነገ​ሬ​ንስ እንደ ኢም​ንት የሚ​ያ​ደ​ር​ገው ማን ነው?”

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መጽ​ሐፈ ኢዮብ 24