YouVersion Logo
Search Icon

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 36

36
ሰና​ክ​ሬም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ እንደ ዛተ
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በን​ጉሡ በሕ​ዝ​ቅ​ያስ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመ​ሸ​ጉት ከተ​ሞች ሁሉ ወጥቶ ወሰ​ዳ​ቸው። 2የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ራፋ​ስ​ቂ​ስን ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላከው፤ እር​ሱም በአ​ጣ​ቢው እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ይ​ኛ​ዪቱ ኵሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆመ። 3የቤ​ቱም አዛዥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እርሱ ወጡ።
4ራፋ​ስ​ቂ​ስም አላ​ቸው፥ “ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ታላቁ የአ​ሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ በማን ትተ​ማ​መ​ና​ለህ? 5በም​ክ​ርና በከ​ን​ፈር ንግ​ግር ጦር​ነት ይሆ​ና​ልን? አሁ​ንም በእኔ ላይ ያመ​ፅ​ኸው በማን ተማ​ም​ነህ ነው? 6እነሆ፥ በዚያ በተ​ቀ​ጠ​ቀጠ በሸ​ን​በቆ በትር በግ​ብፅ ትታ​መ​ና​ለህ፤ ሰው ቢመ​ረ​ኰ​ዘው ተሰ​ብሮ በእጁ ይገ​ባል፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ሁሉ እን​ዲሁ ነው። 7አን​ተም፦ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ታ​መ​ና​ለን ብትል፥ ሕዝ​ቅ​ያስ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ በዚህ መሥ​ዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹ​ንና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያስ​ፈ​ረሰ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?#ግሪክ ሰባ. ሊ. ከዚህ ይለ​ያል። 8አሁን እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተስ​ማማ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶ​ችን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ። 9ከታ​ና​ና​ሾቹ ከጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች የሚ​ያ​ን​ሰ​ውን የአ​ን​ዱን ጭፍራ ፊት መመ​ለስ እን​ዴት ትች​ላ​ለህ? ስለ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች በግ​ብፅ የሚ​ታ​መኑ ለጌ​ታዬ ባሮች ናቸው። 10አሁ​ንም በውኑ ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እና​ጠ​ፋ​ችሁ ዘንድ ወደ​ዚህ ሀገር ዘም​ተ​ና​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ሀገ​ራ​ቸው ዘም​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አ​ቸው” አለን።
11ኤል​ያ​ቄ​ምና ሳም​ናስ፥ ዮአ​ስም ራፋ​ስ​ቂ​ስን፥ “እኛ እን​ሰ​ማ​ለ​ንና እባ​ክህ፥ በሶ​ርያ ቋንቋ ለባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ ተና​ገር፤ በቅ​ጥ​ርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ አት​ና​ገ​ረን” አሉት። 12ራፋ​ስ​ቂስ ግን፥ “ጌታዬ ይህን ቃል እና​ገር ዘንድ ወደ እና​ን​ተና ወደ ጌታ​ችሁ ልኮ​ኛ​ልን? ከእ​ና​ንተ ጋር ኵሳ​ቸ​ውን ይበሉ ዘንድ፥ ሽን​ታ​ቸ​ው​ንም ይጠጡ ዘንድ በቅ​ጥር ላይ ለተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ አይ​ደ​ለ​ምን?” አላ​ቸው።
13ራፋ​ስ​ቂ​ስም ቆሞ በታ​ላቅ ድምፅ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ እን​ዲህ ብሎ ጮኸ፥ “የታ​ላ​ቁን የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ቃል ስሙ። 14ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ ያድ​ና​ችሁ ዘንድ በማ​ይ​ችል ቃል ሕዝ​ቅ​ያስ አያ​ታ​ል​ላ​ችሁ። 15ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ር​ግጥ ያድ​ና​ች​ኋል፤ ይህ​ችም ከተማ በአ​ሦር ንጉሥ እጅ አት​ሰ​ጥም አይ​በ​ላ​ችሁ። 16ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም አት​ስሙ፤ የአ​ሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ በሕ​ይ​ወት ልት​ኖሩ ብት​ወ​ድዱ ሁላ​ችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከወ​ይ​ና​ች​ሁና ከበ​ለ​ሳ​ችሁ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዳ​ች​ሁም ውኃ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ፤ 17ይህም መጥቼ ምድ​ራ​ች​ሁን ወደ​ም​ት​መ​ስ​ለው ምድር፥ እህ​ልና የወ​ይን ጠጅ፥ እን​ጀ​ራና ወይን ወዳ​ለ​ባት ምድር እስ​ካ​ፈ​ል​ሳ​ችሁ ድረስ ነው። 18ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነ​ናል ብሎ አያ​ታ​ል​ላ​ችሁ። በውኑ የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሀገ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ አድ​ነ​ዋ​ቸ​ዋ​ልን? 19የሐ​ማ​ትና የአ​ር​ፋድ አማ​ል​ክት ወዴት አሉ? ሰማ​ር​ያን ከእጄ አድ​ነ​ዋ​ታ​ልን? 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከእጄ ያድን ዘንድ ከእ​ነ​ዚህ ሀገ​ሮች አማ​ል​ክት ሁሉ ሀገ​ሩን ከእጄ ያዳነ አለን?”
21እነ​ር​ሱም ዝም አሉ፤ አን​ዳ​ችም አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም፤ ንጉሡ እን​ዳ​ይ​መ​ል​ሱ​ለት አዝዞ ነበ​ርና። 22የቤቱ አዛዥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ የሠ​ራ​ዊቱ ጸሓፊ ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጡ፤ የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ቃል ነገ​ሩት።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in