ወደ ዕብራውያን 8
8
ስለ ጽድቅ ድንኳን
1 #
መዝ. 109፥1። ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን። 2እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት። 3ሊቀ ካህናት ሁሉ መባንና መሥዋዕትን ያቀርብ ዘንድ ይሾማል፤ ለዚህም ደግሞ የሚያቀርበው አንዳች ነገር ይኖረው ዘንድ ይገባል። 4በምድር ቢሆን ኖሮ፥ ሊቀ ካህናት ባልሆነም ነበር፤ በኦሪት ሕግ መሥዋዕት የሚያቀርቡ ካህናት በእርስዋ አሉና። 5እነርሱም ሙሴ ድንኳኒቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ፤ “በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ” ብሎት ነበርና። 6ዛሬ ግን ኢየሱስ ክርስቶስ የምትበልጠውን አገልግሎት ገንዘብ አደረገ፤ ለታላቂቱ ሥርዐትም መካከለኛ ሆነ፤ የምትበልጠውንም ተስፋ ሠራ። 7ፊተኛይቱ ያለ ነቀፋ ብትሆን ኖሮ ሁለተኛይቱን ባልፈለገም ነበር። 8#ኤር. 31፥31-34። ነገር ግን እነርሱን ነቅፎ እንዲህ አለ፥ “እነሆ፥ ለቤተ እስራኤልና ለቤተ ይሁዳም አዲስ ኪዳን የምሠራበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር። 9እጃቸውን ይዤ ከምድረ ግብፅ ባወጣኋቸው ጊዜ ለአባቶቻቸው እንደ ገባሁት እንደዚያ ያለ ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልኖሩምና፤ እኔም ቸል ብያቸዋለሁና” ይላል እግዚአብሔር። 10ከእነዚያ ዘመናት በኋላ ለቤተ እስራኤል የምገባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በልባቸው አሳድራለሁ፤ በሕሊናቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል ይላል እግዚአብሔር። 11እንግዲህ አንዱ ሌላውን አያስተምርም፤ ወንድምም ወንድሙን እግዚአብሔርን ዕወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና። 12ዐመፃቸውን እምራቸዋለሁና ኀጢአታቸውንም ደግሜ አላስብም።” 13አዲስ ትእዛዝ በማለቱ የቀደመችቱን አስረጃት፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ለጥፋት የቀረበ ነው።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን 8: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in