YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 8

8
ስለ ጽድቅ ድን​ኳን
1 # መዝ. 109፥1። ከተ​ና​ገ​ር​ነ​ውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ዙፋን ቀኝ የተ​ቀ​መጠ እን​ዲህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት አለን። 2እር​ሱም የመ​ቅ​ደ​ስና የእ​ው​ነ​ተ​ኛ​ይቱ ድን​ኳን አገ​ል​ጋይ ነው፤ እር​ስ​ዋም በሰው ሳይ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ተ​ከ​ለች ናት። 3ሊቀ ካህ​ናት ሁሉ መባ​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ያቀ​ርብ ዘንድ ይሾ​ማል፤ ለዚ​ህም ደግሞ የሚ​ያ​ቀ​ር​በው አን​ዳች ነገር ይኖ​ረው ዘንድ ይገ​ባል። 4በም​ድር ቢሆን ኖሮ፥ ሊቀ ካህ​ናት ባል​ሆ​ነም ነበር፤ በኦ​ሪት ሕግ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርቡ ካህ​ናት በእ​ር​ስዋ አሉና። 5እነ​ር​ሱም ሙሴ ድን​ኳ​ኒ​ቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰ​ማ​ያዊ ነገር ምሳ​ሌና ጥላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ “በተ​ራ​ራው እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልህ ምሳሌ ሁሉን ታደ​ርግ ዘንድ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎት ነበ​ርና። 6ዛሬ ግን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ት​በ​ል​ጠ​ውን አገ​ል​ግ​ሎት ገን​ዘብ አደ​ረገ፤ ለታ​ላ​ቂቱ ሥር​ዐ​ትም መካ​ከ​ለኛ ሆነ፤ የም​ት​በ​ል​ጠ​ው​ንም ተስፋ ሠራ። 7ፊተ​ኛ​ይቱ ያለ ነቀፋ ብት​ሆን ኖሮ ሁለ​ተ​ኛ​ይ​ቱን ባል​ፈ​ለ​ገም ነበር። 8#ኤር. 31፥31-34። ነገር ግን እነ​ር​ሱን ነቅፎ እን​ዲህ አለ፥ “እነሆ፥ ለቤተ እስ​ራ​ኤ​ልና ለቤተ ይሁ​ዳም አዲስ ኪዳን የም​ሠ​ራ​በት ዘመን ይመ​ጣል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 9እጃ​ቸ​ውን ይዤ ከም​ድረ ግብፅ ባወ​ጣ​ኋ​ቸው ጊዜ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እንደ ገባ​ሁት እን​ደ​ዚያ ያለ ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ኖ​ሩ​ምና፤ እኔም ቸል ብያ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 10ከእ​ነ​ዚያ ዘመ​ናት በኋላ ለቤተ እስ​ራ​ኤል የም​ገ​ባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በል​ባ​ቸው አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ በሕ​ሊ​ና​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 11እን​ግ​ዲህ አንዱ ሌላ​ውን አያ​ስ​ተ​ም​ርም፤ ወን​ድ​ምም ወን​ድ​ሙን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕወቅ ብሎ አያ​ስ​ተ​ም​ርም፤ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያው​ቁ​ኛ​ልና። 12ዐመ​ፃ​ቸ​ውን እም​ራ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሜ አላ​ስ​ብም።” 13አዲስ ትእ​ዛዝ በማ​ለቱ የቀ​ደ​መ​ች​ቱን አስ​ረ​ጃት፤ አሮ​ጌና ውራጅ የሆ​ነ​ውስ ለጥ​ፋት የቀ​ረበ ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 8