ትንቢተ ሕዝቅኤል 5
5
ሕዝቅኤል ምልክት ሊሆን ጠጕሩን መላጨቱ
1“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ራስን ከሚላጭ ምላጭ ይልቅ የተሳለ ጐራዴን ውሰድ፤ ወስደህም በእርስዋ ራስህንና ጢምህን ተላጭ፤ ሚዛንንም ውሰድ፤ ጠጕሩንም ትከፋፍለዋለህ። 2የእስራትህም ወራት በተፈጸመ ጊዜ በከተማዪቱ መካከል ሢሶውን#በግእዝና በዕብ. ሦስት ጊዜ “ሢሶ” የተባለው በግሪክ ሰባ. ሊ. “ሩብ” ነው። በእሳት ታቃጥላለህ፤ ሢሶውንም ወስደህ ዙሪያውን በጎራዴ ትመታለህ፤ ሢሶውንም ወደ ነፋስ ትበትናለህ፤ እኔም በኋላቸው ጎራዴ እመዝዛለሁ። 3ከዚያም በቍጥር ጥቂቶቹን ውሰድ፤ በመጐናጸፊያህም ቋጥራቸው። 4ከእነርሱም ደግሞ ወስደህ በእሳት ውስጥ ትጥላለህ፤ በእሳትም ታቃጥላቸዋለህ፤ ከእርስዋም እሳት ይወጣል፤ የእስራኤልንም ቤት ሁሉ እንዲህ ትላቸዋለህ።”
5ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህች ኢየሩሳሌም ናት፤ እርስዋንና አውራጃዎችዋንም በአሕዛብ መካከል አድርጌአለሁ፥ 6እርስዋም ከአሕዛብ ይልቅ ፍርዴን በኀጢአት ለወጠች፤ በዙሪያዋም ከአሉ ሀገሮች ሁሉ ይልቅ ትእዛዜን ተላለፈች፤ ፍርዴን ጥለዋልና፥ በትእዛዜም አልሄዱምና። 7ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዙሪያችሁ ላሉት አሕዛብ ሰበብ ሆናችኋልና፥ በትእዛዜም አልሄዳችሁምና፥ ፍርዴንም አልጠበቃችሁምና፥ በዙሪያችሁም እንደ አሉ እንደ አሕዛብ ፍርድ እንኳ አላደረጋችሁምና፥ 8ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ራሴ በአንቺ ላይ ነኝ፤ በአሕዛብም ፊት ፍርድን በመካከልሽ አደርጋለሁ። 9ስለ ርኵሰትሽም ሁሉ ያልሠራሁትን፥ እርሱንም የሚመስል ደግሞ የማልሠራውን ነገር እሠራብሻለሁ። 10ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፤ ፍርድንም አደርግብሻለሁ፤ ከአንቺም የቀረውን ሁሉ ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ። 11ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ዐይኔም አይራራም፤ እኔም ይቅር አልልም። 12ከአንቺም ሢሶው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሩብ” ይላል። በቸነፈር ይሞታል፤ በመካከልሽም በራብ ያልቃል፤ ሢሶውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል፤ ሢሶውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ፤ በኋላቸውም ሰይፍን እመዝዛለሁ።
13“ቍጣዬንና መዓቴንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ፤ መዓቴንም በፈጸምሁባቸው ጊዜ እኔ እግዚአብሔር በቅንዓቴ እንደ ተናገርሁ ታውቂያለሽ። 14በዙሪያሽም በአሉ በአሕዛብ#“በአሕዛብ የሚለው” በዕብ. ብቻ። መካከል በሚያልፉም ሁሉ ፊት ከልጆችሽ ጋር አጠፋሻለሁ። 15በቍጣዬና በመቅሠፍቴ በተበቀልሁሽ ጊዜ በዙሪያሽ በአሉ በአሕዛብ ዘንድ ትጨነቂያለሽ፤ ትደነግጫለሽም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። 16ለማጥፋትም የሆነውን፥ አጠፋችሁም ዘንድ የምሰድደውን የራብ ፍላጻ በላያችሁ በሰደድሁ ጊዜ፥ ራብን እጨምርባችኋለሁ፤ የእንጀራችሁንም በትር እሰብራለሁ። 17ራብንና ክፉዎችን አራዊት እሰድድብሻለሁ፤ እቀሥፍሻለሁ፤ ልጆችሽንም ያጠፋሉ#“ልጆችሽንም ያጠፋሉ” የሚለው በዕብ. ብቻ። ቸነፈርና ደምም በአንቺ ላይ ይመጡብሻል፤ ሰይፍንም አመጣብሻለሁ፤ ይከቡሻልም። እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 5: አማ2000
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in