YouVersion Logo
Search Icon

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 11

11
ጠቢብ ሊያ​ደ​ር​ገው ስለ​ሚ​ገባ ነገር
1እን​ጀ​ራ​ህን በውኃ ፊት ላይ ጣለው፥ ከብዙ ቀን በኋላ ታገ​ኝ​ኘ​ዋ​ለ​ህና። 2ለሰ​ባት፥ ደግ​ሞም ለስ​ም​ን​ት​ዕ​ድል ፈን​ታን ስጥ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ሆ​ነ​ውን ክፉ ነገር ምን እንደ ሆነ አታ​ው​ቅ​ምና። 3ደመ​ናት ዝናም በሞሉ ጊዜ በም​ድር ላይ ያፈ​ስ​ሱ​ታል፤ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወ​ድቅ፥ ዛፉ በወ​ደ​ቀ​በት ስፍራ በዚያ ይኖ​ራል። 4ነፋ​ስን የሚ​ጠ​ባ​በቅ አይ​ዘ​ራም፥ ደመ​ና​ት​ንም የሚ​መ​ለ​ከት አያ​ጭ​ድም። 5የነ​ፋስ መን​ገድ እን​ዴት እንደ ሆነች፥ አጥ​ን​ትም በእ​ር​ጉዝ ሆድ እን​ዴት እን​ድትዋ​ደድ እን​ደ​ማ​ታ​ውቅ፥ እን​ዲ​ሁም ሁሉን የሚ​ሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ አታ​ው​ቅም።
6ይህ ወይም ያ ማና​ቸው እን​ዲ​በ​ቅል ወይም ሁለቱ መል​ካም እንደ ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምና በማ​ለዳ ዘር​ህን ዝራ፥ በማ​ታም እጅ​ህን አት​ተው። 7ብር​ሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሓ​ይ​ንም ማየት ለዐ​ይን መል​ካም ነው። 8ሰው ብዙ ዘመን በሕ​ይ​ወት ቢኖር፥ በሁ​ሉም ደስ ቢለው፤ የጨ​ለ​ማ​ውን ዘመን ያስብ፥ ብዙ ቀን ይሆ​ና​ልና። የሚ​መ​ጣ​ውም ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።
ምክር ለጐ​በ​ዞች
9አንተ ጐበዝ፥ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ደስ ይበ​ልህ፥ በጕ​ብ​ዝ​ና​ህም ወራት ልብ​ህን ደስ ይበ​ለው፥ በል​ብ​ህም መን​ገድ፥ ዐይ​ኖ​ች​ህም በሚ​ያ​ዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለ​ዚህ ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ፍርድ እን​ዲ​ያ​መ​ጣህ ዕወቅ። 10ሕፃ​ን​ነ​ትና ጕብ​ዝና፥ አለ​ማ​ወ​ቅም ከንቱ ናቸ​ውና ከል​ብህ ቍጣን አርቅ፥ ከሰ​ው​ነ​ት​ህም ክፉ ነገ​ርን አስ​ወ​ግድ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in