YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች 4

4
1 # ኤፌ. 6፥9። ጌቶች ሆይ፥ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ችሁ ትክ​ክ​ለ​ኛ​ውን አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እው​ነ​ት​ንም ፍረዱ፤ በሰ​ማይ ጌታ እን​ዳ​ላ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።
ስለ ወን​ጌል መስ​ፋ​ፋት መጸ​ለይ እን​ደ​ሚ​ገባ
2በም​ስ​ጋና እየ​ተ​ጋ​ችሁ ለጸ​ሎት ፅሙ​ዳን ሁኑ። 3ስለ እርሱ የታ​ሰ​ር​ሁ​ለ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሥ​ጢር እን​ድ​ን​ና​ገር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃ​ሉን በር ይከ​ፍ​ት​ልን ዘንድ ለእ​ኛም ደግሞ ጸል​ዩ​ልን፤ ለም​ኑ​ል​ንም፤ 4ልና​ገ​ርም እን​ደ​ሚ​ገ​ባኝ እገ​ል​ጠው ዘንድ ጸል​ዩ​ልኝ። 5#ኤፌ. 5፥16። ዘመ​ኑን እየ​ዋ​ጃ​ችሁ#“ዘመ​ኑን እየ​ዋ​ጃ​ችሁ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ ብቻ። ከሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ ተለዩ ሰዎች በማ​ስ​ተ​ዋል ሂዱ። 6ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​መ​ልሱ ታውቁ ዘንድ ንግ​ግ​ራ​ችሁ ሁል​ጊዜ በጨው እንደ ተቀ​መመ በጸጋ ይሁን።
የመ​ም​ህሩ ዜና በደቀ መዝ​ሙሩ
7 # የሐዋ. 20፥4፤ 2ጢሞ. 4፥12። የተ​ወ​ደደ ወን​ድ​ማ​ች​ንና የታ​መነ አገ​ል​ጋይ፥ በጌታ ሥራም ተባ​ባ​ሪ​ያ​ችን የሆነ ቲኪ​ቆስ የእ​ኔን ዜና ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል። 8#ኤፌ. 6፥21-22። ስለ​ዚህ ሥራ ወደ እና​ንተ የላ​ክ​ሁት ዜና​ዬን ታውቁ ዘንድ፥ ልባ​ች​ሁ​ንም ያጽ​ናና ዘንድ ነው። 9#ፊል. 1፥10-12። ወገ​ና​ችሁ ከሆ​ነው ከም​ን​ወ​ደ​ውና ከታ​መ​ነው ወን​ድ​ማ​ችን ከአ​ና​ሲ​ሞስ ጋር፥ እነ​ርሱ ሥራ​ች​ን​ንና ያለ​ን​በ​ትን ያስ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል።
ሰላ​ምታ ለደቀ መዛ​ሙ​ርት
10 # የሐዋ. 19፥29፤ 27፥2፤ ፊልሞ. 24፤ የሐዋ. 12፥12፤ 25፤ 13፥13፤ 15፥37-39። ከእኔ ጋር የተ​ማ​ረ​ከው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮስ፥ ወደ እና​ንተ በሚ​መጣ ጊዜ ትቀ​በ​ሉት ዘንድ ስለ እርሱ ያዘ​ዝ​ኋ​ችሁ የበ​ር​ና​ባስ የአ​ባቱ ወን​ድም ልጅ ማር​ቆ​ስም፥#ግሪኩ “የበ​ር​ና​ባስ የወ​ን​ድሙ ልጅ” ይላል። 11ኢዮ​ስ​ጦስ የተ​ባለ ኢያ​ሱም፥ ከግ​ዙ​ራን ሰዎች ወገን የሚ​ሆኑ እነ​ዚህ ሰላም ይሏ​ች​ኋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ሥራ ረዳ​ቶች እነ​ዚህ ብቻ ናቸው፤ እነ​ር​ሱም እኔን አጽ​ና​ን​ተ​ው​ኛል። 12#ቈላ​. 1፥7፤ ፊልሞ. 23። ከእ​ና​ንተ ወገን የሚ​ሆን ኤጳ​ፍ​ራ​ስም ሰላም ይላ​ች​ኋል፥ እርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋይ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ወ​ደው ነገር ሁሉ ምሉ​ኣ​ንና ፍጹ​ማን እን​ድ​ት​ሆኑ፥ ስለ እና​ንተ ዘወ​ትር ይጸ​ል​ያል፤ ይማ​ል​ዳ​ልም። 13እጅግ እን​ደ​ሚ​ወ​ዳ​ች​ሁና ስለ እና​ንተ በሎ​ዶ​ቅ​ያና በኢ​ያራ ከተማ ስላ​ሉ​ትም እን​ደ​ሚ​ቈ​ረ​ቈር እኔ ምስ​ክሩ ነኝ። 14#2ጢሞ. 4፥10-11፤ ፊልሞ. 24። ወዳ​ጃ​ችን ባለ መድ​ኃ​ኒቱ ሉቃ​ስም ሰላም ብሎ​አ​ች​ኋል፤ ዴማ​ስም ሰላም ይላ​ች​ኋል። 15በሎ​ዶ​ቅያ ላሉት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንና ለን​ም​ፋን፥ በቤ​ቱም ላለች ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ሰላ​ምታ አቅ​ር​ቡ​ልኝ። 16ይህ​ችን መል​እ​ክት እና​ንተ አን​ብ​ባ​ችሁ፥ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ያነ​ብ​ቡ​አት ዘንድ ወደ ሎዶ​ቅያ ላኩ​አት፤ ዳግ​መ​ኛም እና​ንተ ከሎ​ዶ​ቅያ የጻ​ፍ​ኋ​ትን መል​እ​ክት አን​ብ​ቡ​አት። 17#ፊል. 2። አክ​ር​ጳ​ንም “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሾ​ም​ህ​ባ​ትን መል​እ​ክ​ት​ህን እን​ድ​ት​ፈ​ጽ​ማት ተጠ​ን​ቀቅ” በሉት።
18እኔ ጳው​ሎስ በእጄ ጽፌ ሰላም አል​ኋ​ችሁ፤ እስ​ራ​ቴን አስቡ፤ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።
በሮሜ ተጽፋ በቲ​ኪ​ቆስ እጅ ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች የተ​ላ​ከ​ችው መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች።
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in