YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 4

4
ስለ ሐዋ​ር​ያዊ አገ​ል​ግ​ሎት
1ስለ​ዚህ እንደ ቸር​ነቱ የሰ​ጠን ይህ መል​እ​ክት አለ​ንና አን​ሰ​ለ​ችም። 2ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና። 3ወን​ጌ​ላ​ችን የተ​ሰ​ወረ ቢሆ​ንም እንኳ፥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ባ​ቸው ለሚ​ጠ​ፉት ነው። 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው የክ​ር​ስ​ቶስ የክ​ብሩ ወን​ጌል ብር​ሃን እን​ዳ​ያ​በ​ራ​ላ​ቸው የዚህ ዓለም አም​ላክ#ግእዙ “...እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እም​ላክ ዘለ​ዓ​ለም” ይላል። ልባ​ቸ​ውን አሳ​ው​ሮ​አ​ልና። 5ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ጌታ እንደ ሆነ እን​ሰ​ብ​ካ​ለን እንጂ ራሳ​ች​ንን የም​ን​ሰ​ብክ አይ​ደ​ለም፤ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ብለን ራሳ​ች​ንን ለእ​ና​ንተ አስ​ገ​ዛን። 6#ዘፍ. 1፥3። በጨ​ለማ ውስጥ “ብር​ሃን ይብራ” ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፊት የክ​ብ​ሩን ዕው​ቀት ብር​ሃን በል​ባ​ችን አብ​ር​ቶ​ል​ና​ልና።
በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ስላ​ለው መዝ​ገብ
7ነገር ግን ከእኛ ያይ​ደለ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገኘ ታላቅ ኀይል ይሆን ዘንድ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ይህ መዝ​ገብ አለን። 8በሁሉ መከ​ራን እን​ቀ​በ​ላ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጨ​ነ​ቅም፤ እን​ና​ቃ​ለን፥ ነገር ግን ተስፋ አን​ቈ​ር​ጥም። 9እን​ሰ​ደ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጣ​ልም፤ እን​ወ​ድ​ቃ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጠ​ፋም። 10የክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ በዚህ በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሞት በሥ​ጋ​ችን እን​ሸ​ከ​ማ​ለን። 11በሕ​ይ​ወት የም​ን​ኖር እኛም በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር ስለ ኢየ​ሱስ ክስ​ር​ቶስ ብለን ተላ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን። 12ስለ​ዚ​ህም ሞት በእኛ ላይ፥ ሕይ​ወ​ትም በእ​ና​ንተ ላይ ይሠ​ራል።#ግእዙ “ይእ​ዜሰ ጸንዐ ላዕ​ሌነ ሞት እንዘ ሕይ​ወት ኀቤነ” ይላል።
13 # መዝ. 115፥10። አንድ የእ​ም​ነት መን​ፈስ አለን፤ መጽ​ሐፍ፥ “አመ​ንሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ተና​ገ​ርሁ” እን​ዳለ እኛም አመን፤ ስለ​ዚ​ህም ተና​ገ​ርን። 14ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያስ​ነ​ሣው እርሱ እኛ​ንም እንደ እርሱ እን​ዲ​ያ​ስ​ነ​ሣን፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር በፊቱ እን​ዲ​ያ​ቆ​መን እና​ው​ቃ​ለን። 15ጸጋው በብ​ዙ​ዎች ላይ ትት​ረ​ፈ​ረፍ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የክ​ብሩ ምስ​ጋና ይበዛ ዘንድ ሁሉ ስለ እና​ንተ ነውና።
ስለ ውሳ​ጣ​ዊና አፍ​ኣዊ ሰው​ነት
16ስለ​ዚህ አን​ሰ​ልች፤ በውጭ ያለው ሰው​ነ​ታ​ችን ያረ​ጃ​ልና፤ በው​ስጥ ያለው ሰው​ነ​ታ​ችን ግን ዘወ​ትር ይታ​ደ​ሳል። 17ቀላል የሆ​ነው የጊ​ዜው መከ​ራ​ችን ክብ​ር​ንና ጌት​ነ​ትን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አብ​ዝቶ ያደ​ር​ግ​ል​ና​ልና። 18የማ​ይ​ታ​የ​ውን እንጂ የሚ​ታ​የ​ውን ተስፋ አና​ደ​ር​ግም፤ የሚ​ታ​የው ኀላፊ ነውና፥ የማ​ይ​ታ​የው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሚ​ኖር ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in