YouVersion Logo
Search Icon

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 2

2
1እን​ግ​ዲህ እያ​ዘ​ንሁ ወደ እና​ንተ እን​ዳ​ል​መጣ በልቤ ይህን ወሰ​ንሁ። 2እኔ ካሳ​ዘ​ን​ኋ​ች​ሁማ እኔ ካሳ​ዘ​ን​ሁት በቀር ማን ደስ ያሰ​ኘ​ኛል? 3የእኔ ደስታ የሁ​ላ​ችሁ እንደ ሆነ በሁ​ላ​ችሁ አም​ኛ​ለ​ሁና በመ​ጣሁ ጊዜ ደስ ሊያ​ሰ​ኙኝ ከሚ​ገ​ባ​ቸው ኀዘን እን​ዳ​ያ​ገ​ኘኝ ይህን ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ። 4ከብዙ መከ​ራና ከልብ ጭን​ቀት የተ​ነሣ በብዙ እንባ ይህን ጽፌ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን እጅግ እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እን​ድ​ታ​ውቁ ነው እንጂ እን​ድ​ታ​ዝኑ አይ​ደ​ለም።
5ማንም ያሳ​ዘ​ነኝ ቢሆን፥ እኔን ብቻ ያሳ​ዘነ አይ​ደ​ለም። ከእ​ና​ንተ አንድ ሳይ​ቀር ሁላ​ች​ሁ​ንም አሳ​ዘነ እንጂ፤ አሁ​ንም ሥር​ዐት አላ​ጸ​ና​ባ​ች​ሁም። 6እን​ደ​ዚህ ላለው ሰው ከእ​ና​ንተ ከብ​ዙ​ዎች ያገ​ኘ​ችው ይህች ተግ​ሣጽ ትበ​ቃ​ዋ​ለች። 7ደግ​ሞም እን​ዲህ ያለው ሰው ከኀ​ዘን ብዛት የተ​ነሣ እን​ዳ​ይ​ዋጥ ይቅር ልት​ሉ​ትና ልታ​ጽ​ና​ኑት ይገ​ባል። 8ስለ​ዚ​ህም ከእ​ርሱ ጋር ፍቅ​ርን እን​ድ​ታ​ጸኑ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። 9ስለ​ዚ​ህም በሁሉ ትታ​ዘ​ዙኝ እንደ ሆነ፥ ፈቃ​ዳ​ች​ሁን ዐውቅ ዘንድ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ። 10ይቅር የም​ት​ሉት ቢኖር፥ እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር ይቅር እለ​ዋ​ለሁ፤ እኔም ይቅር ያል​ሁ​ትን በክ​ር​ስ​ቶስ ፊት ስለ እና​ንተ ይቅር ብያ​ለሁ። 11ሰይ​ጣን እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ለን አሳ​ቡን የም​ን​ስ​ተው አይ​ደ​ለ​ምና።
ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ
12ለክ​ር​ስ​ቶ​ስም ወን​ጌል ጢሮ​አዳ በደ​ረ​ስሁ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሩ ተከ​ፈ​ተ​ልኝ። 13#የሐዋ. 20፥1። ወን​ድ​ሜን ቲቶን ስላ​ላ​ገ​ኘ​ሁት ለሰ​ው​ነቴ ዕረ​ፍት አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ተለ​ይች ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄድሁ።
በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ድል ስለ መን​ሣት
14በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘወ​ትር ድል በመ​ን​ሣቱ የሚ​ጠ​ብ​ቀን፥ በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ የዕ​ው​ቀ​ቱን መዓዛ በእኛ የሚ​ገ​ልጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን። 15በሚ​ድ​ኑ​ትና በሚ​ጠ​ፉት ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ር​ስ​ቶስ መዓዛ እኛ ነንና። 16የሞት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸው ለሞት፥ የሕ​ይ​ወት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ለሕ​ይ​ወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚ​ገ​ባው ማነው? 17የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በሌላ ቀላ​ቅ​ለው እን​ደ​ሚ​ሸ​ቅጡ እንደ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምና፤ በቅ​ን​ነት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተላከ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ና​ገ​ራ​ለን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in