YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙረ ዳዊት 84

84
1ለመዘምራን አለቃ፥ በዋሽንት፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
2 # መዝ. 43፥3-4፤ 122፥1። የሠራዊት አምላክ ሆይ፥
ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው!
3 # መዝ. 42፥2-3፤ 63፥2-3፤ 143፥6፤ ኢሳ. 26፥9። ነፍሴ የጌታን አደባባዮች ትወድዳለች ትናፍቅማለች፥
ልቤም ሥጋዬም በሕያው አምላክ ደስ ተሰኘ።
4 # መዝ. 5፥3። ወፍ ለእርሷ ቤትን አገኘች፥
ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች፥ በመሠውያህ አጠገብ፥
የሠራዊት አምላክ ንጉሤም አምላኬም ሆይ፥
5በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፥
ለዓለምና ለዘለዓለምም ያመሰግኑሃል።
6አቤቱ፥ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥
በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው።
7በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ ሲያልፉ የምንጭ ቦታ ያደርጉታል፥
የበልግም ዝናብ በረከትን#84፥7 “ኩሬዎችን ይምላልና” ብልው ይሚተርጉሙም አሉ። ይሰጣልና።
8ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፥
የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።
9የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ አድምጥ።
10 # መዝ. 89፥19። አቤቱ፥ መታመናችንን እይልን፥
ወደ ቀባኸውም#84፥10 ንጉሥ። ፊት ተመልከት።
11ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥
በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥
በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።
12ጌታ አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነው፥
ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፥
ጌታ በቅንነት የሚሄዱትን
ከመልካም ነገር አያስቀራቸውም።
13የሠራዊት አምላክ ሆይ፥
በአንተ የታመነ ሰው ምስጉን ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in