መዝሙረ ዳዊት 83
83
1የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
2 #
መዝ. 10፥1፤ 44፥24፤ 109፥1። አቤቱ፥ በጸጥታ አትቆይ፥#83፥2 ግሪኩ “አንተን የሚመስል ማነው” ይላል።
አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።
3እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥
የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።
4 #
ኤር. 11፥9። ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥
በቅዱሳንህም#83፥4 በዕንቁዎችህ ላይ። ላይ ተማከሩ።
5ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥
ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።
6 #
መዝ. 2፥2። በአንድ ልብ በአንተ ላይ ተማከሩ፥
በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፥
7 #
ዘኍ. 20፥23፤ 1ዜ.መ. 5፥10፤19። የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥
ሞዓብም አጋራውያንም፥
8 #
ዘፀ. 17፥8፤ ኢያ. 13፥2። ጌባል አሞንም አማሌቅም፥
ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፥
9አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥
ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኗቸው።
10 #
ዘፀ. 2፥15፤ ኢሳ. 9፥3፤ 10፥26። እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥
በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው።
11 #
ኤር. 8፥2። በዓይንዶር ጠፉ፥
እንደ ምድርም ጉድፍ ሆኑ።
12አለቆቻቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፥
ታላላቆቻቸውንም እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው፦
13የእግዚአብሔርን መስክ እንወርሳለን የሚሉትን።
14 #
መዝ. 1፥4፤ 35፥5፤ 58፥10፤ ኢሳ. 5፥24፤ 10፥17፤ 17፥13፤ 29፥5፤ ሕዝ. 21፥3። አምላኬ ሆይ፥ እንደ ትቢያ
በነፋስ ፊትም እንደ ገለባ አድርጋቸው።
15 #
መዝ. 50፥3። እሳት ደንን እንደሚያቃጥል፥
ነበልባልም ተራሮችን እንደሚያነድድ፥
16እንዲሁ በቁጣህ አሳድዳቸው፥
በመቅሠፍትህም አስደንግጣቸው።
17ፊታቸውን እፍረት ሙላው፥
አቤቱ፥ ስምህንም ይፈልጋሉ።
18ይፈሩ ለዘለዓለሙም ይታወኩ፥
ይጐስቁሉ ይጥፉም።
19 #
መዝ. 97፥9፤ ዘዳ. 4፥39፤ ዳን. 3፥45። ስምህም “ጌታ”#83፥19 በዕብራይስጥ “አዶናይ” ይላል። እንደሆነ፥
በምድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደሆንህ ይወቁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 83: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in