መዝሙረ ዳዊት 71
71
1 #
መዝ. 31፥2-4። አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፥ ለዘለዓለም አልፈር።#መዝ. 25፥2።
2በጽድቅህ አስጥለኝ ታደገኝም፥
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድነኝም።
3 #
መዝ. 18፥3። ሁልጊዜ የምጠጋበት ዓለት ሁነኝ፥
ጠንካራ መሸሸጊያ፥
ዓለቴና መጠጊያዬ አንተ ነህና።
4 #
መዝ. 140፥2። አምላኬ፥ ከክፉ እጅ፥
ከዓመፀኛና ከግፈኛም እጅ አድነኝ።
5አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥
አቤቱ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።
6 #
መዝ. 22፥11። ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፥
ከእናቴም ሆድ ጀምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፥
ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው።
7ለብዙዎች መደነቂያ ሆንሁ፥
አንተ ግን ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።
8አፌን ምስጋና ሞላ
ሁልጊዜ ክብርህንና እዘምር ዘንድ።
9በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፥
ጉልበቴም ባለቀ ጊዜ አትተወኝ።
10 #
መዝ. 3፥2፤ 22፥8። ጠላቶቹ በላዬ ተናግረዋልና፥
ነፍሴንም የሚሹአት በአንድነት ተማክረዋልና፥ እንዲህም አሉ፦
11“እግዚአብሔር ትቶታል፥
የሚያድነው የለምና ተከትላችሁ ያዙት።”
12 #
መዝ. 22፥20። አምላክ ሆይ፥ ከእኔ አትራቅ፥
አምላኬ ሆይ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
13 #
መዝ. 35፥4፤ 40፥15፤ 70፥3። ነፍሴን የሚቃወሙአት ይፈሩ ይጥፉም፥
ጉዳቴንም የሚፈልጉ እፍረትንና ኃሣርን ይልበሱ።
14እኔ ግን ሁልጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፥
በምስጋናህም ሁሉ ላይ እጨምራለሁ።
15 #
መዝ. 35፥28። መዘርዘር ከምችለው በላይ ቢሆንም፥
አፌ ጽድቅህን ሁልጊዜም ማዳንህን ይናገራል።
16በጌታ ኃይል እገባለሁ፥
አቤቱ፥ ጽድቅህን ብቻ አስባለሁ።
17አምላኬ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፥
እስከ ዛሬም ተኣምራትህን እነግራለሁ።
18 #
መዝ. 22፥31-32፤ 48፥14-15፤ 145፥4፤ ኢሳ. 46፥3-4። እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ፥
ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን
ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ፥
አቤቱ፥ አትተወኝ።
19 #
መዝ. 72፥18፤ 86፥8። አቤቱ፥ ጽድቅህ እስከ አርያም ይደርሳል፥ ታላላቅ ነገሮችን አድርገሃል፥
አምላክ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
20ብዙ ጭንቀትንና መከራን አሳይተኸኛልና፥
ተመለስህ ሕያውም አደረግኸኝ፥
ከምድር ጥልቅም እንደገና አወጣኸኝ።
21ክብሬን ታበዛለህ፥
ተመልሰህም ደስ ታሰኘኛለህ፥
22እኔም በበገና ስለ እውነትህ አመሰግንሃለሁ፥
የእስራኤል ቅዱስ አምላክ ሆይ፥ በመሰንቆ እዘምርልሃለሁ።
23ዝማሬን ባቀርብሁልህ ጊዜ ከንፈሮቼ ደስ ይላቸዋል፥
አንተ ያዳንሃትም ነፍሴ እንዲሁ።
24ጉዳቴን የሚሹ ባፈሩና በተነወሩ ጊዜ
አንደበቴ ደግሞ ሁልጊዜ ጽድቅህን ይናገራል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 71: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in