መዝሙረ ዳዊት 146
146
የሐጌና የዘካርያስ መዝሙር።
1ሃሌ ሉያ።
ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን አመስግኚ።
2 #
መዝ. 103፥1፤ 104፥33። በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ጌታን አመሰግናለሁ፥
በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
3 #
መዝ. 118፥8-9። ማዳን በማይችሉ በአለቆች፥ በሰው ልጅ፥ አትታመኑ።
4 #
መዝ. 90፥3፤ 104፥29፤ 1መቃ. 2፥63፤ ኢዮብ 34፥14-15፤ መክ. 3፥20፤ 12፥7፤ ሲራ. 40፥11፤ ኢሳ. 2፥22። ነፍሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል፥
ያንጊዜ እቅዶቹ በሙሉ ይጠፋሉ።
5የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ
ተስፋውም በጌታ በአምላኩ የሆነ ሰው ምስጉን ነው፥
6 #
መዝ. 121፥2፤ 124፥8፤ ዘፀ. 20፥11፤ የሐዋ. 14፥15፤ ራእ. 14፥7። እርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም፥ በእነርሱ ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፥
እውነትን ለዘለዓለም የሚጠብቅ፥
7 #
መዝ. 68፥7፤ 103፥6፤ ኢሳ. 49፥9፤ 61፥1። ለተበደሉት የሚፈርድ፥
ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው።
ጌታ የታሰሩትን ይፈታል፥
8 #
መዝ. 145፥14። ጌታ የዕውሮችን ዐይን ያበራል፥
ጌታ የወደቁትን ያነሣል፥
ጌታ ጻድቃንን ይወድዳል፥
9 #
መዝ. 68፥6፤ ዘዳ. 10፥18። ጌታ ስደተኞችን ይጠብቃል፥
ወላጆች የሞቱባቸውንና ባልቴቶችን ይቀበላል፥
የክፉዎችንም መንገድ ያጠፋል።
10 #
መዝ. 145፥13፤ ሰቆ.ኤ. 5፥19። ጌታ ለዘለዓለም ይነግሣል፥
ጽዮን ሆይ፥ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው።
ሃሌ ሉያ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 146: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in