መዝሙረ ዳዊት 119
119
አሌፍ።
1 #
መዝ. 1፥1-2፤ 15፥2፤ 112፥1። በመንገዳቸው እንከን የሌለባቸው፥
በጌታም ሕግ የሚመላለሱ ምስጉኖች ናቸው።
2 #
ዘዳ. 4፥29። ሕጉን#119፥2 ዕብራይስጡ ምስክሩን ይላል፤ የእግዚአብሔር ሕግ የእግዚአብሔር ምስክር ነው። የሚጠብቁ፥
በፍጹም ልብ የሚሹት ምስጉኖች ናቸው፥
3ዓመፅንም አያደርጉም፥ በመንገዶቹም ይሄዳሉ።
4ሕጎችህን በሚገባ እንጠብቅ ዘንድ አንተ
አዘዝህ።
5ደንቦችህን ለመጠበቅ
መንገዶቼ ምነው በቀኑ።
6ትእዛዞችህንም ሁሉ ስመለከት
በዚያን ጊዜ አላፍርምና።
7አቤቱ፥ ትክክለኛ ፍርድህን ስማር
በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።
8ሥርዓትህን እጠብቃለሁ፥
በፍጹም አትጣለኝ።
ቤት።
9ጎልማሳ መንገዱን#119፥9 አኗኗሩን። በምን ያነጻል?
ቃልህን በመጠበቅ ነው።
10በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥
ከትእዛዝህ አታርቀኝ።
11አንተን እንዳልበድል፥
ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
12 #
መዝ. 25፥4፤ 27፥11፤ 86፥11፤ 143፥8፤10። አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፥
ደንቦችህን አስተምረኝ።
13ከአፍህ የሚወጡትን ፍርዶች ሁሉ በከንፈሮቼ ደገምኳቸው።
14በብልጽግና እንደሚደሰቱ ሁሉ
በሕጎችህ መንገድ ደስ አለኝ።
15ደንቦችህን አሰላስላለሁ፥
መንገዶችህንም እመለከታለሁ።
16በድንጋጌዎችህ ደስ ይለኛል፥
ቃልህንም አልረሳም።
ጋሜል።
17ለአገስልጋይህ መልካም አድርግለት፤
ሕያው እንድሆን፥ ቃልህንም እንድጠብቅ።
18ዐይኖቼን ክፈት፥
ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ።
19 #
መዝ. 39፥13። እኔ በምድር እንግዳ ነኝ፥
ትእዛዛትህን ከእኔ አትሰውር።
20ፍርዶችህን ሁልጊዜ በመፈለግ ነፍሴ በናፍቆት ደቀቀች።
21ከትእዛዛትህ የሚያፈነግጡተን ትዕቢተኞችንና ርጉማንን ገሠጽህ።
22ሕግህን ጠብቄአለሁና።
ስድብንና ነውርን ከእኔ አርቅ።
23መስፍኖች ደግሞ ተቀምጠው እኔን አሙኝ፥
አገልጋይህ ግን ሕግህን ያሰላስል ነበር።
24ሕግህም ተድላዬ ነው፥
ደንቦችህም አማካሪዎቼ ናቸው።
ዳሌጥ።
25 #
መዝ. 44፥26። ነፍሴ ወደ አፈር ተጠጋች፥
እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
26መንገዶቼን ዘረዘርሁ፥ ሰማኸኝም፥
ደንቦችህን አስተምረኝ።
27የድንጋጌዎችህን መንገድ እንዳስተውል አድርገኝ፥
ተኣምራትህንም አሰላስላለሁ።
28ከኀዘን የተነሣ ነፍሴ በዕንባ ተዋጠች፥
እንደ ቃልህ አጠንክረኝ።
29የሐሰትን መንገድ ከእኔ አርቅ፥
የሕግህንም ጸጋ ስጠኝ፥
30የእውነትህን መንገድ መረጥሁ፥
ፍርድህንም አልረሳሁም።
31አቤቱ፥ ሕግህን ተጠጋሁ፥ አታሳፍረኝ።
32ልቤን ባሰፋኸው ጊዜ፥
በትእዛዞችህ መንገድ ሮጥሁ።
ሄ።
33 #
መዝ. 19፥12። አቤቱ፥ የደንቦችህን መንገድ አስተምረኝ፥
ለትሩፋትም እጠብቀዋለሁ።
34እንዳስተውል አድርገኝ፥ ሕግህንም እንድጠብቅ፥
በፍጹም ልቤም እጠብቀዋለሁ።
35 #
መዝ. 25፥4፤ 27፥11፤ 86፥11፤ 143፥8፤10። እርሷን ወድጃለሁና የትእዛዝህን መንገድ ምራኝ።
36ልቤን ወደ ምስክርህ አዘንብል፥
ወደ ስስትም አይሁን።
37ከንቱ ነገርን እንዳያዩ ዐይኖቼን መልስ፥
በመንገድህ ሕያው አድርገኝ።
38እንዲፈራህ ባርያህን በቃልህ አጽና።
39ፍርድህ መልካም ናትና
የምፈራውን ስድብ ከእኔ አርቅ።
40እነሆ፥ ትእዛዝህን ናፈቅሁ፥
በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ።
ዋው።
41አቤቱ፥ እንደ ቃልህ፥
ምሕረትህና መድኃኒትህ ይምጡልኝ።
42በቃልህ ታምኛለሁና
ለሚሰድቡኝ በነገር እመልስላቸዋለሁ።
43በፍርድህም ታምኛለሁና
የእውነትን ቃል ከአፌ ፈጽመህ አታርቅ።
44ለዘለዓለም ዓለም
ሁልጊዜ ሕግህን እጠብቃለሁ።
45ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና
አስፍቼ እሄዳለሁ።
46በነገሥታት ፊት ምስክርህን እናገራለሁ፥
አላፍርምም፥
47እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።
48እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣለሁ፥
ሥርዓትህንም አሰላስላለሁ።
ዛይ።
49ለባርያህ የሰጠኸውን የተስፋ ቃልህን አስብ።
50ቃልህ ሕያው አድርጎኛልና
ይህች በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።
51ትዕቢተኞች እጅግ ዐመፁ፥
እኔ ግን ከሕግህ አልራቅሁም።
52ከጥንት የነበረውን ፍርድህን አሰብሁ፥
አቤቱ፥ ተጽናናሁም።
53ሕግህን ከተዉ ከኃጢአተኞች የተነሣ ኀዘን ያዘኝ።
54በእንግድነቴ አገር ሥርዓትህ መዝሙር ሆነችኝ።
55አቤቱ፥ በሌሊት ስምህን አሰብሁ፥
ሕግህንም ጠበቅሁ።
56ትእዛዛትህንም ፈልጌአለሁና ይህች ሆነችልኝ።
ሔት።
57ጌታ ድርሻዬ ነው፥
ቃልህን እጠብቃለሁ አልሁ።
58በፍጹም ልቤ ወደ ፊትህ ተማለልሁ፥
እንደ ቃልህ ማረኝ።
59ስለ መንገዶችህ አሰብሁ፥
እግሬንም ወደ ምስክሮችህ መለስሁ።
60ትእዛዝህን ለመጠበቅ ጨከንሁ አልዘገየሁምም።
61የኀጥኣን ገመዶች ተተበተቡብኝ፥
ሕግህን ግን አልረሳሁም።
62ስለ ጽድቅህ ፍርድ፥
በእኩለ ሌሊት አመሰግንህ ዘንድ እነሣለሁ።
63እኔ ለሚፈሩህ ሁሉ፥
ትእዛዝህንም ለሚጠብቁ ባልንጀራ ነኝ።
64 #
መዝ. 33፥5። አቤቱ፥ ምሕረትህ በምድር ሁሉ ሞላች፥
ሥርዓትህን አስተምረኝ።
ጤት።
65አቤቱ፥ እንደ ቃልህ
ለባርያህ መልካም አደረግህ።
66በትእዛዛትህ ታምኛለሁና
መልካም ምክርና እውቀትን አስተምረኝ።
67በፊት ስቼ ከመንገድህ ርቄ ነበር፥
አሁን ግን ቃልህን ጠበቅሁ።
68አቤቱ፥ አንተ ቸር ነህ፥
በቸርነትህም ሥርዓትህን አስተምረኝ።
69የትዕቢተኞች ዓመጽ በላዬ በዛ፥
እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ።
70 #
መዝ. 17፥10፤ 73፥7፤ ኢዮብ 15፥27። ልባቸው እንደ ወተት ረጋ፥
እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል።
71ሥርዓትህን እማር ዘንድ
ያስጨነቅኸኝ መልካም ሆነልኝ።
72ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ
የአፍህ ሕግ ይሻለኛል።
ዮድ።
73እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም፥
እንዳስተውል አድርገኝ፥ ትእዛዛትህንም እማራለሁ።
74በቃልህ ታምኛለሁና
የሚፈሩህ እኔን አይተው ደስ ይላቸዋል።
75አቤቱ፥ ፍርድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥
በእውነትህም እንዳስቸገርኸኝ አወቅሁ።
76ምሕረትህ ለመጽናናቴ ትሁነኝ፥
እንደ ቃልህም ለባርያህ ይሁነው።
77ሕግህ ተድላዬ ናትና
ቸርነትህ ትምጣልኝ፥ በሕይወትም ልኑር።
78ትዕቢተኞች በዓመፅ ጠምመውብኛልና ይፈሩ፥
እኔ ግን ትእዛዝህን አሰላስላለሁ።
79የሚፈሩህና ምስክሮችህን የሚያውቁ ወደ እኔ ይመለሱ።
80እንዳላፍር ልቤ በሥርዓትህ የቀና ይሁን።
ካፍ።
81 #
መዝ. 130፥6። ነፍሴ መድኃኒትህን ናፈቀች፥
በቃልህም ታመንሁ።
82 #
መዝ. 25፥15፤ 123፥1-2፤ 141፥8። መቼ ታጽናናኛለህ እያልሁ
ዐይኖቼ ስለ ቃልህ ፈዘዙ።
83 #
ኢዮብ 30፥30። በጢስ ውስጥ እንዳለ አቁማዳ ሆኛለሁና፥
ሥርዓትህን ግን አልረሳሁም።
84የባርያህ ዘመኖች ስንት ናቸው?
በሚያሳድዱኝስ ላይ መቼ ትፈርድልኛለህ?
85ኃጢአተኞች ጉድጓድ ቆፈሩልኝ፥
አቤቱ፥ እንደ ሕግህ ግን አይደለም።
86ትእዛዛትህ ሁሉ እውነት ናቸው፥
በዓመፅ አሳድደውኛል፥ እርዳኝ።
87ከምድር ሊያጠፉኝ ጥቂት ቀርቶአቸው ነበር፥
እኔ ግን ትእዛዛትህን አልተውሁም።
88እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ፥
የአፍህንም ምስክር እጠብቃለሁ።
ላሜድ።
89 #
ኢሳ. 40፥8። አቤቱ፥ ቃልህ በሰማይ ለዘለዓለም ይኖራል።
90እውነትህ ለልጅ ልጅ ናት፥
ምድርን መሠረትሃት እርሷም ትኖራለች።
91ሁሉም ባርያዎችህ ናቸውና
ቀኑ በትእዛዝህ ይኖራል።
92ሕግህ ተድላዬ ባይሆን፥
ቀድሞ በጉስቁልናዬ በጠፋሁ ነበር።
93በእርሱ ሕያው አድርገኸኛልና
ፍርድህን ለዘለዓለም አልረሳም።
94እኔ የአንተ ነኝ፥ ፍርድህን ፈልጌአለሁና አድነኝ።
95ኃጢአተኞች ያጠፉኝ ዘንድ ጠበቁኝ፥
ምስክርህን ግን መረመርሁ።
96የሥራን ሁሉ ፍጻሜ አየሁ፥
ትእዛዝህ ግን እጅግ ሰፊ ነው።
ሜም።
97አቤቱ፥ ሕግህን እንደምን እጅግ ወደድሁ!
ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።
98ለዘለዓለም ለእኔ ነውና
ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።
99ምስክርህ ትዝታዬ ነውና
ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ።
100 #
ኢዮብ 32፥6፤ ጥበ. 4፥8-9። ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና
ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ።
101ቃልህን እጠብቅ ዘንድ
ከክፉ መንገድ ሁሉ እግሬን ከለከልሁ።
102አስተምረኸኛልና ከፍርድህ አልራቅሁም።
103 #
መዝ. 19፥11። ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው፥
ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።
104ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፥
ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ።
ኖን።
105 #
መዝ. 18፥29፤ ምሳ. 6፥23። ሕግህ ለእግሬ መብራት፥
ለመንገዴ ብርሃን ነው።
106የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።
107እጅግ ተቸገርሁ፥ አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
108 #
መዝ. 50፥14፤ 23፤ ዕብ. 13፥15። አቤቱ፥ ከአፌ የሚወጣውን ቃል ውደድ፥
ፍርድህንም አስተምረኝ።
109ነፍሴ ሁልጊዜ በእጅህ ውስጥ ናት፥
ሕግህን ግን አልረሳሁም።
110ኃጢአተኞች ወጥመድን ዘረጉብኝ፥
ከትእዛዝህ ግን አልሳትሁም።
111የልቤ ደስታ ነውና
ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።
112ለዘለዓለም ለፍጻሜውም
ትእዛዝህን አደርግ ዘንድ ልቤን አዘነበልሁ።
ሳምኬት።
113ዓመፀኞችን ጠላሁ፥ ሕግን ግን ወደድሁ።
114አንተ ረዳቴና መጠጊያዬ ነህ፥
በቃልህም ተማመንሁ።
115 #
መዝ. 6፥9፤ 139፥19፤ ኢዮብ 21፥14። እናንተ ኃጢአተኞች፥ ከእኔ ራቁ፥
የአምላኬንም ትእዛዝ ልፈልግ።
116እንደ ቃልህ ደግፈኝ፥ ሕያውም እሆናለሁ፥
ከተስፋዬም አልፈር።
117እርዳኝ እድናለሁም፥
ሁልጊዜም ሥርዓትህን እመረምራለሁ።
118ምኞታቸው ዓመፃ ነውና
ከሥርዓትህ የሚርቁትን ሁሉ አጐሳቈልሃቸው።
119የምድርን ኃጢአተኞች ሁሉ እንደ ርኩሰት አጠፋሃቸው፥
ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።
120ሥጋዬ አንተን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፥
ከፍርድህ የተነሣ ፈርቻለሁ።
ዔ።
121ፍርድንና ጽድቅን ሠራሁ፥
ለሚያስጨንቁኝ አሳልፈህ አትስጠኝ።
122ባርያህን በመልካም ጠብቀው፥
ትዕቢተኞችም አይጋፉኝ።
123ዐይኖቼ ለማዳንህ፥
ለጽድቅህም ቃል ፈዘዙ።
124ለባርያህ እንደ ምሕረትህ አድርግ፥
ሥርዓትህንም አስተምረኝ።
125እኔ ባርያህ ነኝ፥ እንዳስተውል አድርገኝ፥
ምስክርህንም አውቃለሁ።
126ለጌታ የሥራ ጊዜ ነው፥
ሕግህንም ሻሩት።
127ስለዚህ ከወርቅና ከዕንቁ ይልቅ ትእዛዝህን ወደድሁ።
128ስለዚህ ወደ ትእዛዝህ ሁሉ አቀናሁ፥
የዓመፅንም መንገድ ሁሉ ጠላሁ።
ፌ።
129ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው፥
ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው።
130የቃልህ ፍቺ ያበራል፥
ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል።
131አፌን ከፈትሁ፥ አለከለክሁም፥
ወደ ትእዛዝህ ናፍቄአለሁና።
132 #
መዝ. 25፥16፤ 86፥16። ስምህን ለሚወድዱ እንደምታደርገው ፍርድ፥
ወደ እኔ ተመልከት ማረኝም።
133አካሄዴን እንደ ቃልህ አቅና፥
ኃጢአትም ሁሉ አይግዛኝ።
134ከሰው ግፍ አድነኝ፥
ትእዛዝህንም እጠብቃለሁ።
135በባርያህ ላይ ፊትህን አብራ፥
ሥርዓትህንም አስተምረኝ።
136ሕግህን አልጠበቅሁምና
የውኃ ፈሳሽ ከዐይኖቼ ፈሰሰ።
ጻዴ።
137 #
ጦቢ. 3፥2። አቤቱ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ ፍርድህም ቅን ነው።
138ምስክርህን በጽድቅ አዘዝህ፥
እጅግም ቅን ነው።
139ጠላቶቼ ቃልህን ረስተዋልና
የቤትህ ቅንዓት አቀለጠኝ።
140ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው፥
ባርያህም ወደደው።
141እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ፥
ትእዛዛትህን ግን አልረሳሁም።
142ጽድቅህ የዘለዓለም ጽድቅ ነው፥
ቃልህም እውነት ነው።
143መከራና ችግር አገኙኝ፥
ትእዛዛትህ ግን ተድላዬ ናቸው።
144ምስክርህ ለዘለዓለም ጽድቅ ነው፥
እንዳስተውል አድርገኝ፥ በሕይወትም አኑረኝ።
ቆፍ።
145በፍጹም ልቤ ጮኽሁ፥ አቤቱ፥ ስማኝ፥
ሥርዓትህን እፈልጋለሁ።
146ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አድነኝ፥
ምስክርህንም እጠብቃለሁ።
147ማለዳ ጮኽሁ፥
ቃልህንም ተስፋ አድርጌአለሁ።
148 #
መዝ. 63፥7፤ 77፥7። ቃልህን አስብ ዘንድ
ዐይኖቼ ለመማለድ ቀደሙ።
149አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ ድምፄን ስማ፥
እንደ ፍርድህ ሕያው አድርገኝ።
150በዓመፃ የሚያሳድዱኝ ቀረቡ፥
ከሕግህም ራቁ።
151አቤቱ፥ አንተ ቅርብ ነህ፥
መንገዶችህም ሁሉ ቅኖች ናቸው።
152ከዘለዓለም እንደ መሠረትኸው
ከቀድሞ ጀምሮ ከምስክርህ የተነሣ አወቅሁ።
ሬስ።
153ሕግህን አልረሳሁምና
ችግሬን ተመልከት አድነኝም።
154 #
መዝ. 43፥1። ፍርዴን ፍረድ አድነኝም፥
ስለ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
155መድኃኒት ከኀጥኣን ሩቅ ነው፥
ሥርዓትህን አልፈለጉምና።
156አቤቱ፥ ቸርነትህ እጅግ ብዙ ነው፥
እንደ ፍርድህ ሕያው አድርገኝ።
157ያሳደዱኝና ያስጨነቁኝ ብዙዎች ናቸው፥
ከምስክር ግን ፈቀቅ አላልሁም።
158ቃልህን አልጠበቁምና
ሰነፎችን አይቼ አዘንሁ።
159ትእዛዝህን እንደ ወደድሁ ተመልከት፥
አቤቱ፥ በምሕረትህ ሕያው አድርገኝ።
160የቃልህ መጀመሪያ እውነት ነው፥
የጽድቅህም ፍርድ ሁሉ ለዘለዓለም ነው።
ሳን።
161ገዢዎች በከንቱ አሳደዱኝ፥
ከቃልህ የተነሣ ግን ልቤ ደነገጠብኝ።
162ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።
163ዓመፃን ጠላሁ ተጸየፍሁም፥
ሕግህን ግን ወደድሁ።
164ስለ ጽድቅህ ፍርድ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ።
165ሕግህን ለሚወድዱ ብዙ ሰላም ነው፥
ዕንቅፋትም የለባቸውም።
166አቤቱ፥ ማዳንህን ተስፋ አደርግሁ፥
ትእዛዛትህንም ጠበቅሁ።
167ነፍሴ ምስክርህን ጠበቀች
እጅግም ወደደችው።
168መንገዶቼ ሁሉ በፊትህ ናቸውና
ትእዛዝህንና ምስክርህን ጠበቅሁ።
ታው።
169አቤቱ፥ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትቅረብ፥
እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ።
170ልመናዬ ወደ ፊትህ ትድረስ፥
እንደ ቃልህ አድነኝ።
171ሥርዓትህን አስተምረኸኛልና
ከንፈሮቼ ምስጋናን አወጡ።
172ትእዛዛትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸውና
አንደበቴ ቃልህን ተናገረ።
173ትእዛዛትህን መርጫለሁና
እጅህ የሚያድነኝ ይሁን።
174አቤቱ፥ ማዳንህን ናፈቅሁ፥
ሕግህም ተድላዬ ነው።
175ነፍሴ ትኑርልኝ ታመሰግንህማለች፥
ፍርድህም ይርዳኝ።
176እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ፥
ትእዛዛትህን አልረሳሁምና ባርያህን ፈልገው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 119: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in