መዝሙረ ዳዊት 115
115
1 #
ሕዝ. 36፥22-23። ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥
ነገር ግን ለስምህ
ስለ ጽኑ ፍቅርህና ስለ እውነትህም ክብርን ስጥ።
2 #
መዝ. 79፥10። አሕዛብ፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” ለምን ይበሉ?
3 #
መዝ. 135፥6። አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው፥
የፈቀደውን ሁሉ አደረገ።
4 #
መዝ. 135፥15-19፤ ጥበ. 15፥15-16፤ ኢሳ. 44፥9፤ ኤር. 10፥1-5። የአሕዛብ ጣዖታቶች የወርቅና የብር፥
የሰው እጅ ሥራ ናቸው።#ኢሳ. 40፥19።
5አፍ አላቸው አይናገሩምም፥
ዐይን አላቸው አያዩምም፥
6ጆሮ አላቸው አይሰሙምም፥
አፍንጫ አላቸው አያሸትቱምም፥
7እጅ አላቸው አይዳስሱምም፥
እግር አላቸው አይሄዱምም፥
በጉሮሮአቸውም ድምፅ አያሰሙም።
8የሚሠሩአቸው፥
የሚያምኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
9 #
መዝ. 33፥20፤ 118፥2-4። የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በጌታ ታመኑ፥
ረድኤታቸውና መከታቸው እርሱ ነው።
10የአሮን ቤት ሆይ፥ በጌታ ታመኑ፥
ረድኤታቸውና መከታቸው እርሱ ነው።
11ጌታን የምትፈሩ፥ በጌታ ታመኑ፥
ረድኤታቸውና መከታቸው እርሱ ነው።
12ጌታ አሰበን፥ ይባርከንማል፥
የእስራኤልን ቤት ይባርካል፥ የአሮንንም ቤት ይባርካል።
13ጌታን የሚፈሩትን፥
ትንንሾችንና ትልልቆችን ይባርካል።
14ጌታ በላያችሁ፥
በላያችሁና በልጆቻችሁ ላይ ይጨምር።
15እናንተ ሰማይንና ምድርን በሠራ ጌታ የተባረካችሁ ሁኑ።
16 #
ዘፍ. 1፥28። ሰማያት የጌታ ሰማያት ናቸው፥
ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት።
17 #
መዝ. 6፥6፤ 88፥11፤ ሲራ. 17፥22፤ ኢሳ. 38፥18። አቤቱ፥ ሙታን የሚያመሰግኑህ አይደሉም፥
ወደ ሲኦልም የሚወርዱ ሁሉ፥
18እኛ ሕያዋን ግን ከአሁን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም
ጌታን እንባርካለን።
ሃሌ ሉያ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 115: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in