መጽሐፈ ምሳሌ 2
2
1ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ብትቀበል፥
ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፥
2ጆሮህ ጥበብን እንዲያደምጥ ታደርጋለህ፥
ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ።
3ማመዛዘንን ብትጠራት፥
ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሣ፥
4እርሷንም እንደ ብር ብትፈልጋት፥
እንደ ተደበቀ ዕንቁም ብትሻት፥
5የዚያን ጊዜ ጌታን መፍራትን ትገነዘባለህ፥
የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ።
6 #
ጥበ. 9፥10፤ ሲራ. 1፥1። ጌታ ጥበብን ይሰጣልና፥
ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፥
7እርሱ ለቅኖች ስምረትን ያከማቻል፥
ያለ ነቀፋ ለሚሄዱትም ጋሻ ነው፥
8የፍርድን ጎዳና ይጠብቃል፥
የቅዱሳኑንም መንገድ ያጸናል።
9የዚያን ጊዜ ጽድቅንና ፍርድን
ቅንነትንና መልካም መንገድን ሁሉ ታስተውላለህ።
10ጥበብ ወደ ልብህ ትገባለችና፥
እውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለችና፥
11ማመዛዘን ይጠብቅሃል፥
ማስተዋልም ይከላከልልሃል፥
12ከክፉ መንገድ አንተን ለማዳን፥
ጠማማ ነገርን ከሚናገሩም ሰዎች፥
13እነርሱም በጨለማ መንገድ ለመሄድ
የቀናውን ጎዳና የሚተዉ፥
14ክፉ በመሥራት ደስ የሚላቸው
በጠማማነትም ሐሤትን የሚያደርጉ፥
15መንገዳቸውን የሚጠመዝዙ
አካሄዳቸውንም የሚያጣምሙ ናቸው፥
16ከእንግዳይቱ#2፥16 ከአመንዝራይቱ ሴት ሴት አንተን ለመታደግ፥
ቃሏን ከምታለዝብ ከማትታወቀው ሴት፥
17የወጣትነት ወዳጅዋን የምትተወው ሴት
የአምላክዋንም ቃል ኪዳን የምትረሳዋ፥
18ቤትዋ ወደ ሞት ያዘነበለ ነው፥
አካሄድዋም ወደ ሙታን ጥላ።
19ወደ እርሷ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥
ወደ ሕይወት ጎዳናም አይደርሱም፥
20አንተም በመልካም ሰዎች መንገድ እንድትሄድ
የጻድቃንንም ጎዳና እንድትጠብቅ።
21ቅኖች በምድር ላይ ይቀመጣሉና፥
ፍጹማንም በእርሷ ይኖራሉና፥
22ክፉዎች ግን ከምድር ይጠፋሉ፥
ዓመፀኞችም ከእርሷ#2፥22 ከምድር ይነጠቃሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 2: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in