YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ ነህምያ 4

4
የጠላት ሴራ መጨናገፍ
1ሳንበላጥ፥ ጦብያ፥ ዓረባውያን፥ አሞናውያንና አሽዶዳውያን የሚታደሰው የኢየሩሳሌም ቅጥር ከፍ እያለ#4፥1 እየወጣ እንደ ሄደ፥ የፈረሰውም እየተጠገነ እንደሆነ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቆጡ። 2መጥተው ኢየሩሳሌምን ሊወጉና ሊሸብሩ ሁሉም በአንድነት አሴሩ። 3ወደ አምላካችን ጸለይን፥ በእነርሱም ምክንያት በሌሊትና በቀን በእነሱ ላይ ጠባቂ አቆምን። 4ይሁዳም፦ “የተሸካሚዎች ኃይል ደክሟል፥ ፍርስራሹም ብዙ ነው፤ ቅጥሩን መሥራት አንችልም” አለ። 5ጠላቶቻችንም፦ “በመካከላቸው እስክንገባና እስክንገድላቸው ድረስ፥ ሥራቸውንም እስክናስተጓጉል ድረስ አያውቁም፥ አያዩምም” አሉ። 6በአጠገባቸው የተቀመጡ አይሁድ መጥተው፦ “ከስፍራው ሁሉ ይመጡብናል” ብለው ዐሥር ጊዜ ነገሩን። 7እኔም ከቅጥሩ በስተ ኋላ በኩል ባለው በታችኛው ስፍራ ሰይፋቸውን፥ ጦራቸውንና ቀስታቸውን አስይዤ ሕዝቡን በየወገናቸው አቆምኳቸው። 8አየሁና ተነሣሁ፥ መኳንንቶቹን፥ ሹማምቱንና የተቀረው ሕዝብ፦ “አትፍሩአቸው፤ ታላቁንና የተፈራውን ጌታ አስታውሱ፥ ስለ ወንድሞቻችሁ፥ ስለ ወንዶች ልጆቻች፥ ስለ ሴቶች ልጆቻችሁ፥ ስለ ሚስቶቻችሁና ስለ ቤቶቻችሁ ተዋጉ።” አልኳቸው።
9እንዲህም ሆነ፥ ጠላቶቻችን በእኛ ዘንድ እንደታወቀ፥ እግዚአብሔርም ምክራቸውን ከንቱ እንዳደረገው በሰሙ ጊዜ፥ እኛ ሁላችንም ወደ ቅጥሩ፥ እያንዳንዳችን ወደ ሥራችን ተመለስን። 10#መዝ. 149፥6።ከዚያን ቀን ጀምሮ እኩሌቶቹ ጎልማሶች ሥራ ሲሠሩ፥ እኩሌቶቹ ጋሻ፥ ጦር፥ ቀስትና ጥሩር ይይዙ ነበር፤ ሹማምቱም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር። 11ቅጥሩን የሚሠሩትና ተሸካሚዎቹ በአንድ እጃቸው ይሠሩ፥ በአንድ እጃቸው ደግሞ የጦር መሣሪያ ይይዙ ነበር። 12እያንዳንዱ ግንበኛ ሰይፉን በወገቡ ታጥቆ ይሠራ ነበር፤ ቀንደ መለከትም የሚነፋውም በአጠገቤ ነበረ። 13መኳንንቱን፥ ሹማምቱንና የቀሩትን ሕዝብ እንዲህ አልኋቸው፦ “ሥራው ብዙና ሰፊ ነው፥ እኛም በቅጥሩ ላይ አንዱ ከሌላው ርቆ ተለያይተናል፤ 14የቀንደ መለከቱን ድምፅ በምትሰሙበት ስፍራ በዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል።”
15እኛ ሥራውን ሠራን፤ እኩሌቶቹ ደግሞ ጎሕ ሲቀድ ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ ጦር ይይዙ ነበር። 16እንዲሁም ደግሞ በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፦ “በሌሊት ጠባቂዎች፥ በቀንም ሥራ እንዲሰሩልን እያንዳንዱ ከአገልጋዩ#4፥16 ዕብራይስጡ ጎልማሳው ወይም ወጣቱ ይለዋል። ጋር በኢየሩሳሌም ውስጥ ይደር፤” አልኋቸው። 17እኔ፥ ወንድሞቼ፥ ጎበዛዝቶቼና ከኋላዬ የነበሩት ጠባቂዎች ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። ወደ ውኃም ስንሄድ እያንዳንዱ መሣሪያውን ይዞ ይሄድ ነበር።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in