YouVersion Logo
Search Icon

የማቴዎስ ወንጌል 19

19
መፋታት እንደማይገባ የተሰጠ ትምህርት
(ማር. 10፥1-12)
1ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ፥ ከገሊላ ወጥቶ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ወደ ይሁዳ አውራጃ መጣ። 2ብዙ ሕዝብም ተከተሉት፤ እርሱም እዚያ ፈወሳቸው።
3ፈሪሳውያንም ወደ እርሱ ቀረቡና ሊፈትኑት ፈልገው “ሰው በማንኛውም ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን?” አሉት። 4#ዘፍ. 1፥27፤ 5፥2።እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት እንዳደረጋቸው አላነበባችሁምን? 5#ዘፍ. 2፥24።ዓለም ‘በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።’ 6ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው።” 7#ዘዳ. 24፥1-4፤ ማቴ. 5፥31።እነርሱም “ታዲያ ሙሴ ለምን የፍቺ ወረቀት ሰጥቶ እንዲፈታት አዘዘ?” አሉት። 8እርሱም እንዲህ አላቸው “ሙሴ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ የፈቀደላችሁ በልባችሁ ጥንካሬ ምክንያት ነው፤ ከመጀመሪያው ግን እንዲህ አልነበረም። 9#ማቴ. 5፥32፤ 1ቆሮ. 7፥10፤11።እኔ ግን እላችኋለሁ በዝሙት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን ፈትቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል።”
10ደቀ መዛሙርቱም “የባልና የሚስት ግንኙነት እንዲህ ከሆነስ መጋባት ጥሩ አይደለም” አሉት። 11እርሱ ግን እንዲህ አላቸው “ይህ ንግግር የተሰጠው ካልሆነ በስተቀር ሁሉም አይቀበለውም፤ 12ከእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፤ ሰው የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፤ ለመንግሥተ ሰማያት ሲሉ ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው።”
ኢየሱስ ሕፃናትን እንደ ባረከ
(ማር. 10፥13-16ሉቃ. 18፥15-17)
13በዚያን ጊዜ እጆቹን ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ገሠጹአቸው። 14ነገር ግን ኢየሱስ እንዲህ አለ “ሕፃናቱን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም እንዲመጡ አትከልክሉአቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና።” 15እጆቹን ጫነባቸውና ከዚያ ሄደ።
የሀብታሙ ወጣት ጥያቄ
(ማር. 10፥17-31ሉቃ. 18፥18-30)
16እነሆ አንድ ሰው ቀርቦ “መምህር ሆይ! የዘለዓለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ” አለው። 17እርሱም “ስለ መልካም ነገር እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ከፈልግህ ግን ትእዛዛቱን ጠብቅ፤” አለው። 18#ዘፀ. 20፥13፤ ዘዳ. 5፥17፤ ዘፀ. 20፥14፤ ዘዳ. 5፥18፤ ዘፀ. 20፥15፤ ዘዳ. 5፥19፤ ዘፀ. 20፥16፤ ዘዳ. 5፥20።እርሱም “የትኞቹን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው “አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ 19#ዘፀ. 20፥12፤ ዘዳ. 5፥16፤ ዘሌ. 19፥18።አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ።” 20ወጣቱም “ይህን ሁሉ ጠብቄአለሁ፤ አሁን የሚጐድለኝ ምንድነው?” አለው። 21ኢየሱስም “ፍጹም መሆን ከፈለግህ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፤ በሰማያት መዝገብ ታገኛለህ፤ መጥተህም ተከተለኝ” አለው። 22ወጣቱ ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ።
23ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጸጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ከባድ ነው። 24ደግሜ እላችኋለሁ፤ ባለጸጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል።” 25ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና “ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?” አሉ። 26ኢየሱስ ግን አያቸውና እንዲህ አላቸው “ይህ በሰው ዘንድ የማይቻል ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል።” 27በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ “እነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ የምናገኘው ታዲያ ምንድነው?” አለው። 28#ማቴ. 25፥31፤ ሉቃ. 22፥30።ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ስለተከተላችሁኝ በዳግም ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በዓሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ፥ በዓሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይም ትፈርዳላችሁ። 29ማንም ስለ ስሜ ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘለዓለም ሕይወትንም ይወርሳል። 30#ማቴ. 20፥16፤ ሉቃ. 13፥30።ነገር ግን ብዙዎቹች ፊተኞች ኋለኞች፥ ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in