የማቴዎስ ወንጌል 17
17
የኢየሱስ መልክ መለወጥ
(ማር. 9፥2-13፤ ሉቃ. 9፥28-36)
1ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን ያዕቆብንና ወንድሙ ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን ይዞአቸው ወጣ። 2በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። 3እነሆ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። 4ጴጥሮስም ኢየሱስን “ጌታ ሆይ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትፈቅድስ አንድ ለአንተ፥ አንድ ለሙሴ፥ አንድ ደግሞ ለኤልያስ የሚሆን ሦስት ዳሶችን በዚህ እንሥራ” አለው። 5#ዘፍ. 22፥2፤ መዝ. 2፥7፤ ኢሳ. 42፥1፤ ማቴ. 3፥17፤ 12፥18፤ ማር. 1፥11፤ ሉቃ. 3፥22፤ ዘዳ. 18፥15።#2ጴጥ. 1፥17፤18።እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆ ከደመናው ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የተወደደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ። 6ደቀመዛሙርቱ ይህንን ሰምተው በፊታቸው ወደቁ፤ እጅግም ፈርተው ነበር። 7ኢየሱስም መጥቶ ዳሰሳቸውና “ተነሡ፥ አትፍሩ” አላቸው። 8ዐይኖቻቸውን በገለጡ ጊዜ ግን ከኢየሱስ በቀር ማንንም አላዩም።
9ከተራራው እየወረዱ ሳሉ ኢየሱስ “የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ” ብሎ አዘዛቸው። 10#ሚል. 4፥5።ደቀ መዛሙርቱም “ታዲያ ጻፎች ‘ኤልያስ አስቀድሞ ሊመጣ ይገባዋል’ ለምን ይላሉ?” ብለው ጠየቁት። 11#ሲራ. 48፥10።ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ኤልያስ በእርግጥ ይመጣል፤ ሁሉንም ያስተካክላል፤ 12#ማቴ. 11፥14።ነገር ግን ኤልያስ ከዚህ በፊት መጥቷል እላችኋለሁ፤ ነገር ግን የፈለጉትን ሁሉ አደረጉበት እንጂ አላወቁትም፤ እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ከእነርሱ መከራ ይቀበላል” አላቸው። 13በዚያን ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ስለ መጥምቁ ስለ ዮሐንስ እንደ ነገራቸው አወቁ።
ኢየሱስ ጋኔን ያደረበትን ልጅ እንደ ፈወሰ
(ማር. 9፥14-29፤ ሉቃ. 9፥37-43)
14ወደ ሕዝቡም በመጡ ጊዜ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀረበና ተንበርክኮ 15“ጌታ ሆይ! ልጄን ማርልኝ፥ በሚጥል በሽታ ክፉኛ ይሣቀያል፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ላይ ብዙ ጊዜ ደግሞ በውሃ ውስጥ ይወድቃልና። 16ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት ነገር ግን ሊፈውሱት አልቻሉም” አለው። 17ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ “የማያምንና ጠማማ ትውልድ ሆይ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት” 18ኢየሱስም ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፤ ልጁም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ። 19ከዚህ በኋላ ደቀመዛሙርቱ ብቻቸውን ወደ ኢየሱስ ቀርበው “እኛ ልናስወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?” አሉት። 20#ማቴ. 21፥21፤ ማር. 11፥23፤ 1ቆሮ. 13፥2።እርሱም የእምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ “ከዚህ ወደዚያ ሂድ” ብትሉት ይሄዳል፤ የሚያቅታችሁ ምንም ነገርም የለም። 21እንዲህ ዓይነቱ በጸሎትና በጾም ካልሆነ በቀር ከቶ አይወጣም።
ኢየሱስ ስለ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ዳግመኛ እንደ ተናገረ
(ማር. 9፥30-32፤ ሉቃ. 9፥43-45)
22በገሊላ ተሰባስበው ሳሉ ኢየሱስ “የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፤ 23ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው። እጅግም አዘኑ።
የቤተ መቅደስ ግብር ስለ መክፈል
24 #
ዘፀ. 30፥13፤ 38፥26። ወደ ቅፍርናሆም በደረሱ ጊዜ ሁለት ዲናር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና “መምህራችሁ ሁለት ዲናር#17፥24 ለቤተ መቅደስ ግብር ሁለት ዲናር ይከፈል ነበር። አይከፍልምን?” አሉት። 25“ይከፍላል” አለ። ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ኢየሱስ አስቀድሞ “ስምዖን ሆይ! ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥ ወይም ግብር ከማን ይቀበላሉ? ከልጆቻቸው? ወይስ ከሌሎች?” አለው። 26እርሱም “ከሌሎች” አለው፤ ኢየሱስም “ስለዚህ ልጆች ነጻ ናቸው። 27ነገር ግን እንቅፋት እንዳንሆንባቸው ወደ ባሕር ሂድና መንጠቆ ጣል፥ በመጀመሪያ የሚወጣውን ዓሣ ውሰድ፥ አፉን ስትከፍት እስታቴር#17፥27 እስታቴር ገንዘብ ነው። ታገኛለህ፤ ያን ወስደህ የእኔንና የአንተን ክፈል።”
Currently Selected:
የማቴዎስ ወንጌል 17: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in