YouVersion Logo
Search Icon

የያዕቆብ መልእክት መግቢያ

መግቢያ
ይህ የያዕቆብ መልእክት ለዕለታዊ ኑሮ መመሪያ የሚሆኑ ሐሳቦችን ያዘለ ሲሆን የተጻፈውም በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ዐሥራ ሁለት ነገዶች ነው፤ ጸሐፊው ጥበብን በተግባር ስለምናውልበት ዘዴ፥ ለክርስቲያናዊ አቀባበልና ጠባይ መመሪያ ስለሚሆኑ ነገሮች ግልጥ በሆነ ሥዕላዊ አገላለጽ ያቀርባል። ጸሐፊው ስለ ድህነትና ስለ ሀብት፥ ስለ ፈተና፥ ስለ መልካም ጠባይ፥ ስለ ቅናት፥ ስለ እምነትና በጎ ምግባር፥ ስለ አንደበት ጠቃሚነትና ጐጂነት፥ ስለ ጥበብ፥ እርስ በርስ ስለ መጣላት፥ ስለ ትዕቢትና ስለ ትሕትና፥ በሌሎች ላይ ስለ መፍረድ፥ ስለ ትምክሕት ስለ ትዕግሥትና ስለ ጸሎት፥ ክርስቲያኖች ሊያደርጉት ስለሚገባቸው ግዴታ በዝርዝር ጽፎአል።
መልእክቱ በክርስትና ሕይወት ውስጥ እምነት በተግባር ስለሚተረጐምበት ሁኔታ አጒልቶ ያሳያል። በተጨማሪም የተራራው ስብከት ተብሎ ከሚጠራው የክርስቶስ ትምህርት ጋር በጣም ይመሳሰላል (ማቴዎስ ምዕራፍ 5-7)።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1)
እምነትና ጥበብ (1፥2-8)
ድህነትና ሀብት (1፥9-11)
ፈተና (1፥12-18)
የእግዚአብሔርን ቃል መስማትና ማድረግ (1፥19-27)
አድልዎ እንዳይደረግ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ (2፥1-13)
እምነትና ሥራ (2፥14-26)
ክርስቲያንና አንደበቱ (3፥1-18)
ክርስቲያንና ይህ ዓለም (4፥1—5፥6)
ስለተለያዩ ነገሮች የተሰጠ ምክር (5፥7-20)
ምዕራፍ

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in