ወደ ዕብራውያን መግቢያ
መግቢያ
ይህ መልእክት በደረሰባቸው ከባድ ተቃውሞ የተነሣ እምነታቸውን ሊተዉ የተቃረቡ ክርስቲያኖችን ለማጽናናት ተጻፈ ነው። ትውፊት የዚህ መልእክት ጸሐፊ ጳውሎስ እንደ ያስተምራል። ጸሐፊው የዕብራውያን አማኞችን ለታማኝነት የሚጠራቸው ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛና የመጨረሻው የእግዚአብሔር መገለጥ መሆኑን በማሳየት ነው። እነዚህ ክርስቲያኖች በእምነታቸው እንዲጸኑ ያበረታታቸዋል፤ ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ ሦስት እውነቶችን አጒልቶ ያሳያል፦
1. በተቀበለው መከራ አማካይነት ለአብ እውነተኛ ታዛዥ የሆነው ኢየሱስ ዘላለማዊ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ በመሆኑም ከብሉይ ኪዳን ነቢያት፥ ከሙሴና ከመላእክት እጅግ የላቀ ነው።
2. ኢየሱስ ከብሉይ ኪዳን ካህናት እጅግ የላቀ ዘላለማዊ ካህን መሆኑን እግዚአብሔር ራሱ ተናግሮአል።
3. በኢየሱስ በኩል አማኙ ከኃጢአት፥ ከፍርሃትና ከሞት ይድናል፤ በዕብራውያን የእምነት ሥርዓቶችና የእንስሳት መሥዋዕት እንደ ጥላ የነበረው መዳን ሊቀ ካህናት በሆነው ኢየሱስ አማካኝነት ሙላትንና ፍጻሜን አግኝቷል።
ጸሐፊው በእስራኤል ታሪክ ዝነኞች የሆኑ የእግዚአብሔር ሰዎችን እምነት እንደ ምሳሌ በመጠቀም በምዕራፍ ዐሥራ አንድ አንባቢዎቹ በእምነታቸው እንዲጸኑ ያሳስባቸዋል፤ እንዲሁም በምዕራፍ ዐሥራ ሁለት አንባቢዎቹ ዐይኖቻቸውን በኢየሱስ ላይ በማተኰር በእምነታቸው እንዲጸኑና ማንኛውም ዓይነት መከራና ሥቃይ ቢደርስባቸው እንኳን እንዲታገሡ ይመክራቸዋል፤ በመጨረሻም የምክርና የማስጠንቀቂያ ቃል በመስጠት ይደመድማል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ፦ እግዚአብሔር በክርስቶስ መገለጡ (1፥1-3)
ክርስቶስ ከመላእክት በላይ መሆኑ (1፥4—2፥18)
ክርስቶስ ከሙሴና ከኢያሱ በላይ መሆኑ (3፥1—4፥13)
የክርስቶስ ክህነት የበላይነት (4፥14—7፥28)
የክርስቶስ ቃል ኪዳን ዘላለማዊነት (8፥1—9፥22)
የክርስቶስ መሥዋዕትነት ብልጫ (9፥23—10፥39)
የእምነት ታላቅነት (11፥1—12፥29)
እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት (13፥1-19)
የመዝጊያ ጸሎት (13፥20-21)
ማጠቃለያ (13፥22-25)
ምዕራፍ
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን መግቢያ: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in