2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ መግቢያ
መግቢያ
64 ዓ.ም ገደማ ጳውሎስ በሮሜ እስር ቤት ሳለ ሁለተኛውን መልእክቱን ጽፎአል። በዚያን ወቅት ብዙ የጳውሎስ ወዳጆች ከድተውት ነበር (1፥15-18፤ 4፥9፤18)። በዚህ መልእክት ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ያለውን ጠንካራ ወዳጅነቱንና ወንድማዊ ፍቅሩን ገልጾአል። እንዲሁም ለጢሞቴዎስ የመጨረሻ ቃሉንና ምክሩን የለገሰበት መልእክቱ ነበር። ጳውሎስ ጢሞቴዎስ በእምነት እንዲጸና፥ ያለ ፍርሃት ምእምናንን ከሐሰተኛ አስተማሪዎች እንዲጠብቅ፥ እውነተኛውን የቤተ ክርስትያን አስተምህሮ በምንም ዓይነት ነገር ሳይናወጥ እንዲያስተምር አቅዶ የጻፈው መልእክት ነው ማለት ይቻላል። በእርሱም ዘንድ የነበረውን ዕቃ ጢሞቲዎስ እንዲያመጣለትና በዚያውም እንዲጎበኘው ያሳስበዋል።
ይህ መልእክት የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች በምን ዓይነት መንገድ መመላለስ እንደሚገባቸውና እውነተኛውን አስተምህሮ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ያስተምራል። በመጨረሻ ጢሞቴዎስን በማበረታታት ያለፍርሃትና ያለመናወጥ ከሞት ጽዋ ተካፋይ እንደሚሆን ይመሰክራል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-2)
ለጢሞቴዎስ የተሰጠ ምክር (1፥3—2፥13)
በክሕደት ጊዜ ታማኝ ሆኖ መገኘት (2፥14—4፥5)
በወቅቱ ስለ ነበሩት ሁኔታዎችና አስፈላጊ መመሪያዎች (4፥6-18)
ማጠቃለያ (4፥19-22)
ምዕራፍ
Currently Selected:
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ መግቢያ: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in