2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 10
10
ዳዊት አሞናውያንን ድል አደረገ
1 #
1ዜ.መ. 19፥1-19። ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ሞተ፤ ልጁ ሐኑንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። 2ዳዊትም፥ “አባቱ ቸርነትን እንዳደረገልኝ ሁሉ፥ እኔም ለናዖስ ልጅ ለሐኑን ቸርነት አደርጋለሁ” አለ። ስለዚህ ስለ አባቱ ሞት የተሰማውን ኀዘን እንዲገልጹለት ዳዊት መልክተኞችን ላከ። የዳዊት ሰዎች ወደ አሞናውያን ምድር በደረሱ ጊዜ፥ 3የአሞናውያን መኳንንት፥ ጌታቸው ሐኑንን፥ “ዳዊት የተሰማውን ኀዘን ለመግለጽ ሰዎች መላኩ አባትህን ለማክበር አስቦ ይመስልሃል? የላካቸው ሰዎች ከተማዪቱን እንዲመረምሩ፥ እንዲሰልሉና እንዲያጠፏት አይደለምን?” አሉት። 4#ኢሳ. 20፥4።ስለዚህ ሐኑን የዳዊትን አገልጋዮች ይዞ፥ የእያንዳንዳቸውን ጢም በከፊል ላጨ፥ ልብሳቸውንም ወገባቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ሰደዳቸው። 5ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፥ ሰዎቹ እጅግ ዐፍረው ስለ ነበር መልክተኞቹን ላከባቸው፤ ንጉሡም፥ “ጢማችሁ እስኪያድግ በኢያሪ፥ ቆዩና ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው።
6 #
2ሳሙ. 8፥3፤ 1ሳሙ. 14፥47። አሞናውያን፥ ዳዊት እንደጠላቸው ባወቁ ጊዜ፥ ከቤትረሖብና ከጾባ ሃያ ሺህ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም ንጉሥ መዓካን ከአንድ ሺህ ሰዎቹ ጋር ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ቀጠሩ። 7#2ሳሙ. 11፥1።ዳዊት ይህን ሲሰማ፥ ኢዮአብን ከመላው ተዋጊ ሠራዊት ጋር ላከው። 8አሞናውያን ወጥተው በከተማቸው መግቢያ በር ላይ ተሰለፉ፤ የጾባና የረሖብ ሶርያውያን እንዲሁም የጦብና የመዓካ ሰዎች ለብቻ ሜዳው ላይ ተሰለፉ።
9ኢዮአብም ከፊትና ከኋላው ጦር እንደ ከበበው ባየ ጊዜ፥ በእስራኤል ጀግንነታቸው ከታወቀው ጥቂቶቹን መርጦ በሶርያውያን ግንባር አሰለፋቸው። 10የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ ሥር መድቦ በአሞናውያን ግንባር አሰለፋቸው። 11ኢዮአብም እንዲህ አለ “ሶርያውያን የሚያይሉብኝ ከሆነ አንተ መጥተህ ትረዳኛለህ፤ አሞናውያን የሚያይሉብህ ከሆነ ደግሞ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ። 12እንግዲህ በርታ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ ጌታም በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ።” 13ከዚያም ኢዮአብና አብሮት የነበረው ሠራዊት ሶርያውያንን ለመውጋት ወደ ፊት ገሠገሠ፤ ሶርያውያንም ከፊቱ ሸሹ። 14ሶርያውያን መሸሻቸውን አሞናውያን ባዩ ጊዜ፥ እነርሱም ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማዪቱ ውስጥ ገቡ። ስለዚህም ኢዮአብ አሞናውያንን መውጋቱን አቁሞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
15 #
2ሳሙ. 8፥3-8፤ 1ዜ.መ. 9፥16-19። ሶርያውያን በእስራኤላውያን እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ፥ እንደገና ተሰባሰቡ። 16ሀዳድዔዜር መልክተኞችን ሰዶ ከወንዙ ማዶ ያሉትን ሶርያውያን አስመጣ፤ እነርሱም በሀዳድዔዜር ሠራዊት አዛዥ በሾባክ መሪነት ወደ ሔላም ሄዱ። 17ለዳዊት ይህ በተነገረው ጊዜ፥ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ። ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤ 18ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደለባቸው። እንዲሁም የሠራዊታቸውን አዛዥ ሾባክን አቁስሎት ስለ ነበር እዚያው ሞተ። 19በሀዳድዔዜር ሥር የነበሩት ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል መሸነፋቸውን ባዩ ጊዜ ከእስራኤላውያን ጋር ሰላም መሠረቱ፤ ተገዙላቸውም። ከዚያም በኋላ ሶርያውያን ዳግመኛ ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈሩ።
Currently Selected:
2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 10: መቅካእኤ
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in