YouVersion Logo
Search Icon

1ኛ መጽሐፈ መቃብያን 11

11
ጰጠሎሜዎስ (6ኛው) እስክንድር ድል መታ፤ ዳግማዊ ዲሜጥሮስ ሞተ
1የግብጽ ንጉሥ ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የሆነ ሠራዊትና ብዙ የጦር መርከቦችን ጨምሮ የእስክንድርን መንግሥት በተንኮል በእራሱ መንግሥት ላይ ጨምሮ ለመያዝ ፈለገ፤ 2የሰላም መግለጫ በመስጠት ወደ ሦርያ ሄደ፤ የከተማዎቹ ሰዎች በሮቻቸውን ከፈቱለትና ሊቀበሉት ወጡ፤ ንጉሥ እስክንድር አማቹን እንዲቀበሉ ስላዘዘዛቸው ተቀበሉት። 3ጰጠሎሜዮስ ወደ ከተማይቱ እንደ ገባ ወዲያውኑ ጠባቂ ወታደሮች በየከተማው አደረገ። 4ወደ አዛጦን ለመድረስ በተቃረበ ጊዜ የዳጐን ቤት መቃጠሉን፥ አዛጦንና አካባቢዎችዋ መደምሰሳቸውን፥ ሬሳዎች በዚህም በዚያም መጣላቸውን፥ ንጉሡ በሚያልፍበት ቦታ ሰብስበውና ደራርበው አስቀምጠዋቸው ስለ ነበር በውጊያው ጊዜ ተቃጥለው የነበሩትን ሰዎች ቅሪቶቻቸውንም አሳዩት። 5ለማስወቀስ ሲሉ ዮናታን ያደረገውን ገለጡለት፤ እርሱ ግን ዝም አለ፤ 6ዮናታን ንጉሡን በታላቅ ክብር ለመቀበል ወደ ኢዮጲ መጣ፤ ሰላምታ ተሰጣጡና በዚያ ቦታ አብረው አደሩ። 7ዮናታን ኤለውጥሮስ እስከሚባለው ወንዝ ድረስ ንጉሡን ሸኝቶ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ። 8ንጉሥ ጰጠሎሜዮስ በበኩሉ በባሕሩ አጠገብ እስከምትገኘው ስለውቅያ ድረስ በባሕሩ ዳር ዳር የሚገኙትን ከተሞች ያዘ፤ በእስክንድርም የሚሸርበውን ሴራ ከፍተኛ ደረጃ ላይ አደረሰው። 9ወደ ንጉሥ ዲሜጥሮስ ልጄን በሚስትነት እሰጥሃለሁ፤ በአባትህ መንግሥትም ላይ ትነግሣለሁ። 10እርሱ እኔን ለመግደል ስለፈለገ ልጄን ለእርሱ መስጠቴ አሳዝኖኛል። 11መንግሥቴን መውሰድ ይመኝ ነበር በማለት ወቀሰው። 12ሴት ልጁን ከእስክንድር ወሰደና ለዲመትሪዮስ ሰጠ፤ ከእስክንድር ጋር የነበረውን ግንኙነት አቋረጠ፤ ጥላቸውም እየተባባሰ ሄደ። 13ጰጠሎሜዮስ ወደ አንጾኪያ ገባና የእስያን ዘውድ ደፋ፤ በዚህ ዓይነት የግብጽንና የእስያን ዘውዶች ተቀዳጀ። 14በዚያን ጊዜ ንጉሥ እስክንድር በኪልቂያ ይገኝ ነበር፤ምክንያቱም በአካባቢው ሰዎች አምጸውበት ነበር። 15የተደረገውን በሰማ ጊዜ ከጰጠሎሜዮስ ጋር ለመዋጋት ሄደ፤ ጰጠሎሜዎስም ሽሽቶ ሄደ፤ ንጉሥ ጰጠሎሜዮስ ጋር ለመዋጋት ሄደ፤ ጰጠሎሜዎስም ከብዙ ሠራዊት ጋር ሆኖ ተንቀሳቀሰና ድል መታው። 16እስክንድር ወደ አረብ አገር ሸሽቶ ሄደ፤ ንጉሥ ጰጠሎሜዮስ አሸነፈው። 17ዘብድኤል የሚባል አረባዊ ሰው ግን የእስክንድርን ራስ ቆርጦ ለጰጠሎሜዮስ ላከለት። 18ከሦስት ቀን በኋላ ግን ጰጠሎሜዮስም ሞተ፤ በምሽጉ ውስጥ የነበሩ ወታደሮችም በነዋሪው ሕዝብ ተገደሉ። 192ኛው ዲሜጥሮስ በመቶ ስልሳ ሰባት ዓመተ ዓለም ነገሠ።
የዮናታንና ዲሜጥሮስ ግንኙነት መጀመር
20በእነዚያ ቀኖች ዮናታን የኢየሩሳለምን ምሽግ ከብቦ ለመውጋት የይሁዳን አገረ ሰዎች ሰበሰበ፤ በዚያ ብዙ የጦር ተሸከርካሪ አዘጋጀ። 21በዚያን ጊዜ ሃይማኖት የሌላቸውና ሕግን የሚያከብሩ፥ ሕዝባቸውን የሚጠሉ ሰዎች ሄደው ዮናታንን የኢየሩሳሌምን ምሽግ እንደሚወጋ ለንጉሡ ነገሩት። 22ይህን በሰማ ጊዜ ዲሜጥሮስ ተቆጥቶ ወደ ጰጦሎማይዳ ሄደ፤ ዮናታን ምሽጉን ከመክበብ እንዲቆጠብና በጰጦሎማይዳ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር በፍጥነት እንዲመጣ ጸፈለት። 23ይህን በሰማ ጊዜ ዮናታን ምሽጉን እንዲከቡ አዘዘ፤ አንዳንድ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና አንዳንድ ካህናትን መረጠ፤ እርሱ ራሱም በአደጋው ተጋፈጠ። 24ብር፥ ወርቅ፥ ልብሶችንና ሌሎችም እጅ መንሻዎች በብዛት ይዞ ንጉሡ ወዳለበተ ወደ ጰጦሎማይዳ ሄደ፤ በንጉሡም ፊት ሞገስ አገኘ። 25ከሕዝቡ አንዳንድ ክፉ ሰዎች ሊከሱት ብዙ ሙከራ አደረጉ፤ 26ነገር ግነ ንጉሡ ከእርሱ በፊት እንደነበሩት ነገሥታት ሁሉ አደረገለት፤ በወዳጆቹም ፊት ከፍ ከፍ አደረገው። 27ሊቀ ካህነቱንና በፊት የነበረውን ክብር ሁሉ አጸናለት፤ ከመጀመሪያዎቹ ወዳጆቹ ጋር እንዲቆጠረም አደረገው። 28ዮናታን ለንጉሡ ሦስት መቶ መክሊት ለመስጠት ቃል በመግባት የይሁዳን አገርና የሰማሪያ ሦስት አውራጃዎችን ከግብር ነጻ እንዲያወጣቸው ጠየቀው፤ 29ንጉሡ በዚህ ተስማምቶ እንዲህ ሲል ለዮናታን ጻፈለት፤
አይሁዶችን የሚጠቅም ደንብ ወጣ
30“ንጉሡ ዲሜጥሮስ ለወንድሙ ለዮናታን፤ ለአይሁድ ሕዝብ ሰላምታ ያቀርባል፤ 31ለዘመዳችን ለላስቴን የጻፍነው ደብዳቤ እናንተ እንድታውቁት ግልባጩ ለእናንተ ተልኳል፤ 32ንጉሡ ዲሜጥሮስ ለአባቱ ለላስቴን ሰላምታ ያቀርባል። 33ለእኛ ጥሩ አስተሳሰብ ላላቸው ወዳጆቻችን ለሆኑትና በእኛ ዘንድ በቅን መንፈስ ለሚመሩት አስተሳሰብ ላላቸው ወዳጆቻችን ለሆኑትና በእኛ ዘንድ በቅን መንፈስ ለሚመሩት ለአይሁድ ሕዝብ መልካም ነገርን ለማድረግ ወስነናል፤ 34የይሁዳ አገርና ሦስቱን አገርና በኢየሩሳሌም መሥዋዕት ለሚያቀርቡ ሰዎች ጥቅም እንዲውሉ እነዚህ አውራጃዎች በአካባቢያቸው ከሚገኙ አገሮች ሁሉ ጋር ከሰማርያ ተነጥለዋል፤ ቀድሞ ንጉሥ በየዓመቱ ይቀበላቸው የነበሩት የመሬታቸውና የዛፎቻቸው ፍሬዎች ግብሮች ለእነርሱ ይሆናሉ፤ 35ከጨው ምድር በላይ ለእኛ ይሰጥ ከነበረው ዓሥራትና ከልዩ ልዩ ግብሮች እንዲሁም ከዘውድ ቀረጥ ከአሁን ጀምሮ ነጻ ይሆናሉ። 36እነዚህ ስጦታዎች መቼም፥ የትም ደግሞ አይነሱም። 37እንግዲህ እናንተ የዚህን ደብዳቤ ግልባጭ ለማድረግ ትጉ፥ በቅዱስ ተራራ ላይ በታወቀው ቦታ እንዲቀመጥ ለዮናታን ይሰጠው”።
የዳግማዊ ዲሜጥሮስ በዮናታን ወታደሮች ብርታት በአንጾኪያ ከሞት መትረፍ
38ንጉሥ ዲሜጥሮስ በሥሩ ያለው አገር በሰላም የሚገኝ መሆኑንና ሥልጣኑን የሚቃወም ምንም አለመኖሩን በማየት ሠራዊቱን ሁሉ አሰናብቶ እያንዳንዳቸው ወደመጡበት እንዲሄዱ አደረገ፤ ከእርሱ ጋር የቀሩት ከአሕዛብ ደሴት የቀጠራቸው የውጭ አገር ወታደሮች ብቻ ነበሩ። 39በዚህ ምክንያት ከአባቶቹ ጋር የነበረ አንድ ትሪፎን የተባለ ሰው ሠራዊቱ በጠቅላላ በዲሜጥሮስ ላይ ማጐረምረማቸውን በተገነዘበ ጊዜ የእስክንድርን ልጅ አንጥዮኩስን ወደ ሚያሳድገው ወደ ዓረባዊው ኤማልቄስ ሄደ። 40በአባቱ ቦታ ላይ ልጁ እንዲነግሥ ለእርሱ ልጁን እንዲያስረክበው ወተወተው፤ ዲማጥሮስ የዘዘውን ሁሉ አብራራለት፤ ወታደሮቹም ምን ያህል እንደሚጠሉት ነገረው፤ እዚያ ብዙ ቀኖች ተቀመጠ። 41ንጉሡ ዲሜጥሮስ ከኢየሩሳሌም ምሽግና ከሌሎችም ምሽጐች ወታደሮቹን እንዲያስወጣ የሚነግሩለትን ሰዎች ዮናታን ወደ ንጉሡ ላከ፤ ምክንያቱም ወታደሮቹ ሁልጊዜ ለእስራኤል ጋር በመዋጋት ላይ ነበሩ። 42ዲሜጥሮስ እንዲህ ሲል መልስ ላከ፤ “ለአንተና ለሕዝብህ የማደርገው ይህን ብቻ ሳይሆን ጊዜ ሳገኝ አንተንና ሕዝብህን በክብር ከፍ አደርጋችኋለሁ። 43ለጊዜው አሁን ከጐኔ ተሰልፈው የሚዋጉ ሰዎች በትልክልኝ ደግ ነው፤ ምክንያቱም ወታደሮቼ ሁሉ ከድተውኛል።” 44ዮናታን በጀግንነት የሚዋጉ ሦስት ሺህ ወታደሮች ወደ አንጾኪያ ላከለት፤ ንጉሡም ስለ ደረሱለት ደስ አለው። 45ቁጥራቸው አንድ መቶ ሃያ ሺህ የሚያህል የከተማ ሰዎች ንጉሡን ለመግደል ፈልገው በከተማው መሀል ተሰበሰቡ። 46የከተማው ሰዎች መንገዶቹን በወረሩ ጊዜና ውጊያውም በተጀመረ ጊዜ ንጉሡ አምልጦ ወደ ቤተ መንግሥቱ ገባ፥ 47ንጉሡ አይሁዳውያንን እንዲረዱት ጠራቸው፤ እነርሱ ሁሉ በአጠገቡ ተሰበሰቡ፤ በዚያ ቀን በከተማው ብዙ ሺ ሰው ገደሉ። 48ብዙ ምርኮ ከሰበሰቡ በኋላ በዚያኑ ቀን ከተማውን በእሳት አጋዩ፤ ንጉሡንም ከሞት አወጡት። 49አይሁዳውያን ከተማውን እነደፈለጉት መያዛቸውን ባዩ ጊዜ ሰዎቹ ተስፋ ቆርጠው ወደ ንጉሡ ጮሁ፤ 50“ቀኝ እጅህን ስጠን፤ አይሁዳውያን በእኛ ላይና በከተማው ላይ የሚያደርጉትን ውጊያ እንደያቆሙ አድርግልን” ሲሉ ለመኑት። 51የጦር መሣሪያዎቻቸውን ጥለው ሰላም አደረጉ። አይሁዳውያን በንጉሡና በመንግሥቱ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ሁሉ ፊት ብዙ ክብር አገኙ። በዚህ ዓይነት ዝና አትርፈው አይሁዳውያን ብዙ ምርኮ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። 52ንጉሥ ደሜጥሮስ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ሀገሩም በእርሱ አመራር ሥር በሰላም ኖረ። 53ለዮናታን የገባለትን ቃል ሁሉ አጠፈ፤ ዮናታን ስላደረገለት በጎ ነገር ሁሉ ወሮታውን ካለመከፈሉም ባሻገር በየአቅጣጫው ያርቀው ጀመር።
የዮናታንና የዳግማዊ ዲሜጥሮስ ግጭት፤
የቤተሱር በስምዖን መያዝ፤
የአጾሩ አጋጣሚ
54ከዚህ በኋላ ትሪፎን ተመልሶ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ገና በወጣትነቱ የነገሠውና ዘውድ የደፋው አንጥዮኩስ ነበር። 55ዲሜጥሮስ ያሰናበታቸው ወታደሮቹ ሁሉ አንጥዮኩስ ዙሪያ ተሰበሰቡ፤ ዲሜጥሮስን ወጉትና ሸሹ፤ ድል ተመታ። 56ትሪፎን ዝሆኖቹን ወሰደ፤ አንጾኪያንም ያዘ። 57ወጣቱ አንጥዮኩስ ለዮናታን እንዲህ ሲል ጻፈለት “የሊቀ ካህናቱን ሹመት አጽንቼልሃለሁ፤ በአራቱ አውራጃዎች ላይ ሾሜሃለሁ፤ ቍጥር ህ ከንጉሥ ወዳጆች መካከል እንዲሆን አድርጌአለሁ”። 58የወርቅ ዕቃዎችም ላከለት፤ በወርቅ ጽዋዎች እንዲጠጣ፥ ከፋይ እንዲለብስ፥ የወርቅ መቆለፊያም እንዲኖረው ሥልጣን ሰጠው። 59ወንድሙን ሰምዖንን ከታየር መሰላሎች እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ አስተዳዳሪ እንዲሆን ሾመው። 60ዮናታን መጥቶ ከኤፍራጥስ ከወንዝ ወዲያ ማዶ ያለውን አገርና ከተሞችን እየተዘዋወረ ተመለከተ፤ የሶሪያ አገር ወታደሮች በሙሉ ከእርሱ ጋር ሆነው ለመዋጋት አጠገቡ ተሰለፉ፤ ወደ አስቃሎን መጠ፤ የእዚያ ነዋሪዎች ሁሉ በታላቅ ክብር ተቀበሉት። 61ከዚያ ወደ ጊዛ ሄደ፤ የከተማው ሕዝብ በሩን ዘጋበት፤ ከተማዋን ከበባት፤ ዙሪያዋንም በእሳት አጋየ፤ ዘረፉዋትም። 62የገዛ ሰዎቹ ዮናታንን ለመኑት፤ እርሱም ቀኝ እጁን ዘረጋላቸው፤ ነገር ግን የሹማምንቶቻቸውን ልጆች በመያዣነት ያዘባቸውና ወደ ኢየሩሳሌም ላካቸው ከዚህ በኋላ እስከ ደማስቆ ድረስ እየተዘዋወረ ተመለከተ። 63የዲመትሪዮስ የጦር መሪዎች ዲመትሪዮስን ከግዛቱ ሊያወርዱት ፈልገው በገሊላ በምትገኘው ቃዲስ አጠገብ ከብዙ ሠራዊት ጋር ሆነው መገኘታቸውን ዮናታን ሰማ። 64ከእነርሱ ጋር ለመገናኘት ወደ እነርሱ ሄደ፤ በሀገሩ ወንድሙን ስምዖንን ተወው፤ 65ስምዖንን ወደ ቤተሱር ሄዶ ሰፈረ፤ ዙሪያዋን ከቦና ዘግቶ ብዙ ቀኖች ተዋጋ፤ 66የእዚያ አገር ነዋሪዎች ሰላም ያደርግ ዘንድ ለመኑት፤ ተቀበላቸውም፤ ግን ከተማዋን አስለቀቃቸውና ከእዚያ አስወጣቸው፤ ቦታውን ያዘና እዚያው ወታደሮቹን ለጥበቃ መደበ፤ 67ዮናታንና ሠራዊቱ ግን በጌሣሬጥ ሐይቅ ዳር ላይ ሰፍረው ነበር፤ በማለዳ ተነሥተው ወደ ኀዞር ሜዳ ደረሰ። 68መጀመሪያ በተራራው ላይ የግድያ ወጥመድ ካጠመዱ በኋላ ወራሪ ጦራቸውን በሜዳው ላይ እንዲወጋቸው ላኩበቸው። 69ይህም የሆነው ዋናው የጦር ክፍላቸው በአይሁዳውያን ላይ ጥቃቱን በሚፈጽምበት ወቅት ነው። 70የሠራዊቱ አለቆች የአቤሰሎም ልጅ ማታትያስን፥ የቃልፊ ልጅ ይሁዳ እነዚህ ሁለቱ ብቻ ሲቀሩ ሌላ ማንም ሳይቀር የዮናታን ወታደሮች በሙሉ ሸሹ። 71ዮናታን በኀዘን ልብሱን ቀደደና በራሱ ላይ አመድ ነስንሶ ጸለየ። 72ከዚህ በኋላ ውጊያ ገጠሣቸው፤ አሸነፋቸውና ሸሹ። 73ይህን ባዩ ጊዜ እነዚያ ሸሽተው የነበሩት ሰዎች እንደገና ከእርሱ ጋር ሆነው እስከ ቃዴስ ድረስ አባረሩዋቸው፤ የጠላት ሠፈር እስከሆነው ቃዴስም ድረስ አሳደዋቸው፤ ከእዚያው ሠፈሩ። 74በዚያን ቀን ከውጭ አገር ሠራዊት ሦስት ሺህ ሰዎች ያህል ሞቱ። ዮናታንም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in