YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 99

99
እግዚአብሔር ታላቅ ንጉሥ ነው
1እግዚአብሔር ነገሠ፤
ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤
በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋኑ ተቀመጠ፤
ምድርም ትናወጥ። #ዘፀ. 25፥22።
2እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤
በሕዝቦች ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።
3የአንተን ታላቅና አስፈሪ ስም ያመስግኑ!
እርሱ ቅዱስ ነው።
4ፍትሕን የምትወድ ኀያል ንጉሥ ሆይ!
ቅንነትን መሥርተሃል፤
በእስራኤል ዘንድ ፍትሕንና ጽድቅን ተግባራዊ አድርገሃል።
5አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑት!
በእግሩ ማረፊያ ሥር ስገዱ!
እርሱ ቅዱስ ነው።
6ሙሴና አሮን የእርሱ ካህናት ነበሩ፤
ሳሙኤልም ወደ እርሱ ከጸለዩት አንዱ ነው፤
እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤
እርሱም ሰማቸው።
7በደመና ዐምድ ሆኖ ተናገራቸው፤
የሰጣቸውንም ደንብና ድንጋጌ ፈጸሙ። #ዘፀ. 33፥9።
8እግዚአብሔር አምላክ ሆይ!
ጸሎታቸውን ሰማሃቸው፤
ይቅር ባይ አምላክም ሆንክላቸው፤
ነገር ግን ስለ በደላቸው እነርሱን ከመቅጣት
ቸል አላልክም።
9አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና፥
እርሱን አክብሩት፤
በተቀደሰው ተራራም ላይ ስገዱለት፥

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in