መጽሐፈ መዝሙር 8
8
የእግዚአብሔር ታላቅነትና የሰው ክብር
1ጌታችንና እግዚአብሔር ሆይ!
ስምህ በዓለም ሁሉ የገነነ ነው።
ክብርህንም ከሰማያት ሁሉ በላይ አድርገሃል።
2በጠላቶችህ ምክንያት
ጠላትንና ተበቃይን ዝም ለማሰኘት
ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ አፍ፥ ምስጋናን አዘጋጀህ። #ማቴ. 21፥16።
3አንተ የፈጠርከውን ሰማይ በማይበት ጊዜ፥
በየስፍራቸው አጽንተህ ያኖርካቸውን
ጨረቃንና ኮከቦችን በምመለከትበት ጊዜ፥
4አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
እርሱንስ ትጐበኘው ዘንድ
የሰው ልጅ ምንድን ነው? #8፥4፤ ኢዮብ 7፥17-18፤ መዝ. 144፥3፤ ዕብ. 2፥6-8።
5ከመላእክት በጥቂቱ ብታሳንሰውም፥
የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንክለት፤ #8፥5 ከመላእክት፦ ሌሎች ትርጒሞች ከእግዚአብሔር ይላሉ።
6በፈጠርካቸው ፍጥረቶች ሁሉ ላይ፥
ገዢ አድርገህ ሾምከው፤
ከፍጥረትም ሁሉ በላይ አደረግኸው። #1ቆሮ. 15፥27፤ ኤፌ. 1፥22፤ ዕብ. 2፥8።
7በጎችንና ከብቶችን፥ የዱር አራዊትንም፥
8የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣዎችን፥
በባሕር ውስጥ ያሉ ፍጥረቶችን ሁሉ አስገዛህለት።
9ጌታችን እግዚአብሔር ሆይ!
ስምህ በዓለም ሁሉ የገነነ ነው!
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 8: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997