YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 58

58
እግዚአብሔር ክፉ ሰዎችን እንዲቀጣ የቀረበ ጸሎት
1እናንተ ገዢዎች!
በትክክል ትናገራላችሁን?
በሰዎችስ መካከል ያለ አድልዎ ትፈርዳላችሁን?
2አይደለም! በልባችሁ ክፉ ነገርን ታቅዳላችሁ፤
በምድር ላይ የምትፈጽሙትም ሁሉ የዐመፅ ሥራ ነው።
3ክፉዎች ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ በድለዋል፥
ሐሰትንም ተናግረዋል።
4እነርሱ እንደ እባብ መርዘኞች ናቸው፤
እንደ ደንቆሮ እፉኝትም ጆሮአቸውን ይደፍናሉ።
5እፉኝት ጆሮውን የሚደፍነው
የእባብ አፍዛዦችን ድምፅ፥
ወይም የአስማተኞችን ድግምት ላለመስማት ነው።
6አምላክ ሆይ! የእነዚህን እንደ አንበሳ አስፈሪ የሆኑ ሰዎች ጥርስ ስበር፤
መንጋጋቸውንም አውልቅ።
7ፈስሶ እንደሚያልቅ ውሃ ይጥፉ፤
በመንገድ ላይ እንደ በቀለ ሣር ተረጋግጠው ይርገፉ፤
8እየሄደ ሟምቶ እንደሚያልቅ ቀንድ አውጣና
ሞቶ እንደ ተወለደና ብርሃንን ከቶ እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ።
9እሾኽ በእሳት ላይ ተደርጎ ከመሞቁ በፊት
ፈጥነህ ጠራርገህ አጥፋቸው።
10ኃጢአተኞችን ሲበቀልላቸው በማየታቸው
ጻድቃን ደስ ይላቸዋል፤
በክፉዎችም ደም እግሮቻቸውን ይታጠባሉ።
11በዚያን ጊዜ ሰዎች “ጻድቃን የመልካም
ሥራቸውን ዋጋ አገኙ፤
በዓለም ላይ የሚፈርድ አምላክ
በእርግጥ አለ” ይላሉ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መጽሐፈ መዝሙር 58