YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 46

46
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው
1እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤
ችግር በሚደርስብን ጊዜ ሁሉ ረዳታችን ነው።
2ስለዚህ ምድር ብትናወጥ፥
ተራራዎች ወደ ጥልቅ ባሕር ቢወድቁ፥
3ባሕሮች ታውከው ድምፃቸውን ቢያሰሙ፥
በእነርሱም የእንቅስቃሴ ኀይል
ተራራዎች ቢንቀጠቀጡ አንፈራም።
4ጅረቶችዋ የልዑል እግዚአብሔርን ቅዱስ ማደሪያ፥
የአምላክን ከተማ የሚያስደስቱ አንዲት ወንዝ አለች።
5እግዚአብሔር ከእርስዋ ጋር ስለ ሆነ
ያቺ ከተማ አትናወጥም፤
ጠዋት በማለዳ እግዚአብሔር ይረዳታል።
6ሕዝቦች ተሸበሩ፤
ነገሥታትም ወደቁ፤
እግዚአብሔር ድምፁን ባሰማ ጊዜ
ምድር ቀለጠች።
7የሠራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤
የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
8ኑ፥ የእግዚአብሔርን ሥራ እዩ፤
በምድር ላይ ያመጣውን ጥፋት ተመልከቱ።
9እርሱ በመላው ዓለም የሚካሄደውን
ጦርነት ሁሉ ያቆማል፤
ቀስትንና ጦርን ይሰብራል፤
ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል።
10ጸጥ ብላችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ዕወቁ፤
በሕዝቦች መካከል ከፍ ከፍ እላለሁ፤
በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።
11የሠራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤
የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መጽሐፈ መዝሙር 46