መጽሐፈ መዝሙር 4
4
እግዚአብሔርን በመታመን የሚቀርብ ጸሎት
1አንተ የእውነት አምላክ ነህ፤
እባክህን ለጸሎቴ መልስ ስጠኝ!
እኔ በጣም በጭንቀት ላይ ነበርኩ
አንተ ግን ነጻ አወጣኸኝ፤
አሁንም ራራልኝና ጸሎቴን ስማ።
2እናንተ ሰዎች፥
እስከ መቼ ክብሬን ታዋርዳላችሁ?
እስከ መቼስ ከንቱ ነገርን ትወዳላችሁ?
እስከ መቼስ ሐሰትን ትፈልጋላችሁ?
3እግዚአብሔር ታማኞች የሆኑ ሰዎችን ለራሱ እንደ መረጠ ዕወቁ፤
ስለዚህ ወደ እርሱ በምጸልይበት ጊዜ ይሰማኛል።
4ምንም ያኽል ብትበሳጩ ኃጢአት አትሥሩ፤
በምትተኙበት ስፍራ
በጸጥታ ልባችሁን መርምሩ። #ኤፌ. 4፥26።
5ለእግዚአብሔር ትክክለኛውን መሥዋዕት አቅርቡ፤
እምነታችሁንም በእርሱ ላይ አድርጉ።
6“መልካሙን ነገር ማን ያሳየናል?”
የሚሉ ብዙዎች ናቸው፤
ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ! የፊትህ ብርሃን
በእኛ ላይ ይብራ!
7ሌሎች ከእህልና ከወይን ከሚያገኙት ደስታ ይልቅ
አንተ በልቤ ያኖርከው ደስታ ይበልጣል።
8እግዚአብሔር ሆይ!
በሰላም እንድኖር የምታደርገኝ አንተ ብቻ ስለ ሆንክ
እኔ በምተኛበት ጊዜ፥
በሰላም አንቀላፋለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 4: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997