YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 29

29
የዳዊት መዝሙር
የእግዚአብሔር የድምፁ ኀይል
1እናንተ የሰማይ መላእክት ሁሉ፥
ክብርና ኀይል የእግዚአብሔር ነው በሉ።
2ክብር ለእግዚአብሔር መሆኑን ግለጡ፤
በቅድስናና በግርማ ሞገስ ለተመላ አምላክ ስገዱ። #መዝ. 96፥7-9።
3የእግዚአብሔር ድምፅ በውቅያኖሶች ላይ ያስተጋባል፤
የክብር አምላክ እግዚአብሔር
ከሚናወጠው ማዕበል በላይ ያንጐደጒዳል።
4የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤
ድምፁም ባለ ግርማ ነው።
5የእግዚአብሔር ድምፅ የሊባኖስን ዛፍ ይሰብራል፤
እግዚአብሔር የሊባኖስን ዛፍ ይሰብራል።
6የሊባኖስን ተራራዎች እንደ እንቦሳ
እንዲፈነጩ ያደርጋቸዋል፤
የስርዮንንም ተራራ
እንደ ጐሽ ጥጃ እንዲዘል ያደርገዋል።
7የእግዚአብሔር ድምፅ
መብረቅን ብልጭ ያደርጋል።
8የእግዚአብሔር ድምፅ በረሓን ያናውጣል፤
የቃዴስንም በረሓ ያንቀጠቅጣል፤
9የእግዚአብሔር ድምፅ አጋዘንን እንድትወልድ ያደርጋል
የዛፎችን ቅጠል ያረግፋል፤
በመቅደሱም ያሉ ድምፁን ሲሰሙ
“ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” ይላሉ።
10እግዚአብሔር የጥልቁ ባሕር ገዢ ነው፤
በንጉሥነቱም ለዘለዓለም ይገዛል።
11እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይልን ይሰጣል፤
በሰላም ይባርካቸዋል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መጽሐፈ መዝሙር 29