YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 21

21
ስለ ተገኘው ድል የቀረበ ምስጋና
1አምላክ ሆይ! ኀይልን ስለ ሰጠኸው ንጉሥ ደስ ብሎታል፤
ድልን ስለ አቀዳጀኸውም ሐሴት ያደርጋል።
2የልቡን ምኞት ሰጥተኸዋል፤
የለመነህንም አልከለከልከውም።
3በብዙ በረከትን ሰጥተህ ተቀበልከው፤
በራሱ ላይ የንጹሕ ወርቅ ዘውድ ደፋህለት።
4ሕይወትን እንድትሰጠው ለመነህ፤
አንተም ረጅም ዕድሜና
ዘለዓለማዊ የሆነ ሕይወትን ሰጠኸው።
5አንተ በሰጠኸው ድሎች ምክንያት ታላቅ ክብር አገኘ፤
ክብርንና ግርማን አቀዳጀኸው።
6የዘለዓለም በረከትን ሰጠኸው፤
አንተም ከእርሱ ጋር በመገኘትህ ደስ ታሰኘዋለህ፤
7ንጉሡ የሚተማመነው በእግዚአብሔር ነው፤
የማያቋርጠው የልዑል እግዚአብሔር ፍቅር
ከእርሱ ጋር ስለ ሆነም አይናወጥም።
8እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ፥
ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ሁሉ ያገኛል።
9በምትገለጥበት ጊዜ ከምድጃ እንደሚወጣ
የእሳት ነበልባል ታቃጥላቸዋለህ፤
እግዚአብሔር በቊጣው ወላፈን ይለበልባቸዋል፤
እሳትም ይበላቸዋል።
10ትውልዳቸውን ከምድር ላይ ታጠፋለህ፤
ዘራቸውንም ከሕዝቦች መካከል ለይተህ ትደመስሳለህ።
11በአንተ ላይ ክፉ ነገር ለማድረግ
ቢያቅዱና ቢያድሙም ምንም አይሳካላቸውም።
12ፍላጻዎችህን በእነርሱ ላይ ታነጣጥራለህ፤
ወደ ኋላም ተመልሰው እንዲሸሹ ታደርጋለህ።
13እግዚአብሔር ሆይ! ልዕልናህ ከፍ ከፍ ይበል፤
ስለ ታላቁ ኀይልህም የምስጋና መዝሙር እናቀርባለን።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መጽሐፈ መዝሙር 21