መጽሐፈ መዝሙር 138
138
የምስጋና ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! በሙሉ ልቤ አመሰግንሃለሁ፤
በመላእክት ፊት ለአንተ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።
2ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህና ስለ እውነተኛነትህ
የስምህንና የትእዛዞችህን ከፍተኛነት ስላሳየህ
ወደ ተቀደሰው ቤተ መቅደስህ እየሰገድኩ
ስምህን አመሰግናለሁ።
3በጠራሁህ ጊዜ ሰማኸኝ፤
በብርታትህም አበረታኸኝ።
4እግዚአብሔር ሆይ!
የቃልህን ተስፋ ስለ ሰሙ
የዓለም ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል።
5ስላደረግኸው ድንቅ ነገር ሁሉና ስለ ታላቅ ክብርህ
ይዘምሩልሃል።
6ከሁሉ በላይ ከፍ ያልክ ሆነህ ሳለ፥
ትሑታንን ትንከባከባለህ፤
ትዕቢተኞችን ግን ከሩቅ ሆነህ ትመለከታቸዋለህ።
7መከራ ዙሪያዬን በሚከበኝ ጊዜ
መከታ ሆነህ በሕይወት ትጠብቀኛለህ፤
በቊጣ የተነሡብኝ ጠላቶቼን ትቃወማቸዋለህ፤
በኀይልህም ትታደገኛለህ።
8የገባኸውን ቃል ኪዳን ትፈጽምልኛለህ፤
እግዚአብሔር ሆይ! ፍቅርህ ዘለዓለማዊ ነው፤
የእጅህን ሥራ ወደ ፍጻሜ ሳታደርስ አትተወው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 138: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997