YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 127

127
ስለ እግዚአብሔር ቸርነት የቀረበ ምስጋና
1እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥
የቤት ሠሪዎች ድካም ከንቱ ነው፤
እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥
የከተማ ጠባቂዎች ትጋት ከንቱ ነው።
2በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ
ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤
እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች
ገና ተኝተው ሳሉ
የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል።
3ልጆች ከእግዚአብሔር የሚገኙ ስጦታዎች ናቸው፤
እውነተኛም በረከት ናቸው።
4ሰው በወጣትነቱ የሚወልዳቸው ወንዶች ልጆች
በወታደር እጅ እንዳሉ ፍላጻዎች ናቸው።
5እንደነዚህ ፍላጻዎች የሆኑ ብዙ ልጆች
ያሉት ሰው የታደለ ነው፤
ከጠላቶቹ ጋር በፍርድ አደባባይ
በሚከራከርበት ጊዜ ከቶ አይሸነፍም።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in