YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ መዝሙር 11

11
በእግዚአብሔር መታመን
1እግዚአብሔር ከለላዬ ነው፤
እንዴት “እንደ ወፍ ወደ ተራራዎች ሽሽ” ትሉኛላችሁ።
2ኃጢአተኞች በጨለማ አድብተው
ልበቅኖችን ለመግደል ቀስታቸውን ገትረዋል፤
ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋል።
3መሠረቶች ሲፈርሱ
ጻድቅ ሰው ምን ማድረግ ይችላል?
4እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ ነው፤
ዙፋኑም በሰማይ ነው፤
የሰውን ልጆች ይመለከታል።
አተኲሮም በማየት
ዐይኖቹም ይመረምሩአቸዋል።
5እግዚአብሔር ጻድቃንንና ኃጢአተኞችን ይፈትናል፤
ዐመፅ የሚወዱትን ግን ይጠላቸዋል።
6በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል፤
የሚጋረፍ ነፋስም የእነርሱ ዕድል ፈንታ ነው።
7እግዚአብሔር ጻድቅ ስለ ሆነ የጽድቅን ሥራ ይወዳል፤
ትክክለኛ ሥራ የሚሠራ ሰው ሁሉ ፊቱን ያያል።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

Videos for መጽሐፈ መዝሙር 11