YouVersion Logo
Search Icon

የማቴዎስ ወንጌል 3

3
የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት
(ማር. 1፥1-8ሉቃ. 3፥1-18ዮሐ. 1፥19-28)
1በዚያን ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ በረሓ እየሰበከ መጣ። 2ሲያስተምርም “እነሆ! የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” ይል ነበር። #ማቴ. 4፥17፤ ማር. 1፥15።
3“ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፥
ጥርጊያውንም አቅኑ!’ እያለ በበረሓ የሚጮኽ ሰው ድምፅ” #ኢሳ. 40፥3።
ብሎ ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ስለ ዮሐንስ ነበር።
4የዮሐንስ ልብስ ከግመል ጠጒር የተሠራ ነበር፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የጣዝማ ማር. ነበር፤ #2ነገ. 1፥8፤ ዘካ. 13፥4፤ ዘሌ. 11፥22። 5በዚያን ጊዜ ከኢየሩሳሌም ከመላው የይሁዳ ምድር፥ ከዮርዳኖስም ዙሪያ ሁሉ፥ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይመጡ ነበር። 6ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ፥ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ይጠመቁ ነበር።
7ነገር ግን፥ ዮሐንስ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የእባብ ልጆች! ከሚመጣው ቊጣ እንድታመልጡ ማን አስጠነቀቃችሁ? #ማቴ. 12፥34፤ 23፥33። 8እንግዲያውስ ንስሓ መግባታችሁን የሚያመለክት ሥራ ሥሩ። 9‘እኛ የአብርሃም ልጆች ነን’ በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል እላችኋለሁ። #ዮሐ. 8፥33። 10አሁን ግን፥ መጥረቢያ በዛፎች ሥር ተቀምጦአል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ፥ ተቈርጦ ወደ እሳት ይጣላል። #ማቴ. 7፥19። 11እነሆ፥ እኔ ለንስሓ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤ እርሱ ከእኔ እጅግ ይበልጣል፤ እኔ የእግሩን ጫማ እንኳ ለመሸከም የተገባሁ አይደለሁም። 12እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”
የኢየሱስ መጠመቅ
(ማር. 1፥9-11ሉቃ. 3፥21-22)
13በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ፥ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ። 14ዮሐንስም “ይህስ አይሆንም፤ እኔ በአንተ እጅ መጠመቅ ሲገባኝ፥ እንዴት አንተ ወደ እኔ ትመጣለህ!” ብሎ ይከለክለው ጀመር።
15ኢየሱስ ግን “የጽድቅን ሥራ ሁሉ በዚህ መንገድ መፈጸም ስለሚገባን፥ አሁንስ ተው፤ እንዲሁ ይሁን” ሲል መለሰለት። ዮሐንስም በነገሩ ተስማምቶ ኢየሱስን አጠመቀው። 16ኢየሱስ ተጠምቆ ወዲያውኑ ከውሃው እንደ ወጣ ሰማይ ተከፈተ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በርግብ አምሳል ወርዶ በኢየሱስ ላይ ሲያርፍ አየ። 17በዚያኑ ጊዜ “እነሆ፥ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ። #ዘፍ. 22፥2፤ መዝ. 2፥7፤ ኢሳ. 42፥1፤ ማቴ. 12፥18፤ 17፥5፤ ማር. 1፥11፤ ሉቃ. 9፥35።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in