መጽሐፈ ኢያሱ 12
12
ሙሴ ድል ያደረጋቸው ነገሥታት
1እስራኤላውያን ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንኤም ተራራ ድረስ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ አራባ ሁሉ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምሥራቅ በኩል አሸንፈው ምድራቸውን የያዙባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ 2በሐሴቦን ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን ነበር፤ ግዛቱም የገለዓድን እኩሌታ በማጠቃለል፥ በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከምትገኘው ከዓሮዔር ተነሥቶ በዚያ ሸለቆ መካከል ያለችውን የዐሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ይደርስ ነበር፤ 3እርሱም በምሥራቅ በኩል ከዮርዳኖስ ሸለቆ የገሊላ ባሕር ድረስ፥ በቤት የሺሞት አቅጣጫ እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ ከጨው ባሕር ወደ ደቡብ እስከ ፒስጋ ተራራ ታች ድረስ ያለውን ያጠቃልላል።
4እንዲሁም ከረፋያውያን ወገን የቀረው በአስታሮትና በኤድራይ ይኖር የነበረው የባሳን ንጉሥ ዖግ ነበር፤ 5ግዛቱም የሔርሞንን ተራራ፥ ሳለካን፥ እስከ ገሹርና ማዕካ ድንበሮች የሚደርሰውን የባሳንን ምድር ሁሉ ጠቅልሎ፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሲሖን ይዞታ እስከሆነው ግዛት የገለዓድን እኩሌታ የሚጨምር ነበር። #ዘኍ. 21፥21-35፤ ዘዳ. 2፥26—3፥11።
6እንግዲህ እነዚህ ሁለት ነገሥታት በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴና በእስራኤል ሕዝብ ጦርነት ድል ሆነው ነበር፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም ይህን ምድር ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው። #ዘኍ. 32፥33፤ ዘዳ. 3፥12።
ኢያሱና ድል የነሣቸው ነገሥታት
7ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ባለው ምድር የነበሩትን ነገሥታት ሁሉ ድል ነሡ፤ ይህም ምድር በሊባኖስ ሸለቆ ከሚገኘው ከባዓልጋድ ተነሥቶ በደቡብ በኩል በኤዶም አጠገብ እስካለው እስከ ሐላክ ተራራ ይደርስ ነበር፤ ኢያሱም ይህን ምድር በማከፋፈል ለእያንዳንዱ ነገድ ርስት አድርጎ ሰጠ። 8ይህም የርስት ድርሻ ኮረብታማውን አገር በስተ ምዕራብ ያለውን የኮረብታ ግርጌ፥ የዮርዳኖስን ሸለቆና በእርሱም ኮረብታዎች ግርጌ ያሉትን በስተ ምሥራቅ በኩል የሚገኘውን ረባዳ ቦታና በደቡብ በኩል የሚገኘውን በረሓማ ምድር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ ይህም ምድር ቀድሞ የሒታውያን፥ የአሞራውያን፥ የከነዓናውያን፥ የፈሪዛውያን፥ የሒዋውያንና የኢያቡሳውያን መኖሪያ ነበር። 9የእስራኤል ሕዝብ ንጉሦቻቸውን ድል ነሥተው የያዙአቸውም ከተሞች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፥ ኢያሪኮ፥ በቤትኤል አጠገብ ያለችው ዐይ፥ 10ኢየሩሳሌም፥ ኬብሮን፥ 11ያርሙት፥ ላኪሽ፥ 12ዔግሎን፥ ጌዜር፥ 13ደቢር፥ ጌዴር፥ 14ሖርማ፥ ዐራድ፥ 15ሊብና፥ ዐዱላም፥ 16ማቄዳ፥ ቤትኤል፥ 17ታፑሐ፥ ሔፌር፥ 18አፌቅ፥ ላሻሮን፥ 19ማዶን፥ ሐጾር፥ 20ሺምሮንመሮን፥ አክሻፍ፥ 21ታዕናክ፥ መጊዶ፥ 22ቄዴሽ፥ በቀርሜሎስ የሚገኘው ዮቅነዓም፥ 23በባሕር ጠረፍ የሚገኘው ዶር፥ በጌልገላ የሚገኘው ጎይምና 24ቲርጻ ሲሆኑ፥ ነገሥታቱም በሙሉ ሠላሳ አንድ ነበሩ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 12: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997