YouVersion Logo
Search Icon

መጽሐፈ ኢዮብ 13

13
1“እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዐይኔ አይቶታል፤
ጆሮዬም ሰምቶ አስተውሎታል።
2እናንተ የምታውቁትን ያኽል እኔም ዐውቃለሁ፤
ከቶ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።
3ነገር ግን የእኔ ንግግር ከኀያሉ እግዚአብሔር ጋር ነው፤
ከእርሱ ጋርም እከራከራለሁ።
4እናንተ ግን በሐሰት የተሞላችሁ ናችሁ፤
ማንንም መፈወስ እንደማይችሉ
ሐኪሞች ናችሁ።
5ይልቅስ ዝም ብትሉ ኖሮ
ጠቢባን መስላችሁ በታያችሁ ነበር!
6“የማቀርበውን ክርክር ስሙ፤
በደሌንም ስዘረዝር በጸጥታ አድምጡ።
7በእግዚአብሔር ስም ስለምን ሐሰት ትናገራላችሁ?
በማታለል እግዚአብሔርን የምታስደስቱ ይመስላችኋልን?
8ለእርሱ ታደሉለታላችሁን?
ለእርሱስ ጥብቅና ትቆማላችሁን?
9እግዚአብሔር ቢመረምራችሁ
አንዳች መልካም ነገር ያገኝባችኋልን?
ሰዎችን እንደምታሞኙ እግዚአብሔርንም ማሞኘት
የምትችሉ ይመስላችኋልን?
10በስውር አድልዎ ብታደርጉ
በእውነት እግዚአብሔር ይገሥጻችኋል።
11ክብሩ አያስፈራችሁምን?
ግርማውስ አያስደነግጣችሁምን?
12ምሳሌያዊ አነጋገራችሁ እንደ ዐመድ ዋጋ ቢሶች ናቸው፤
ክርክራችሁም እንደ ሸክላ ተሰባብሮ ይወድቃል።
13እስቲ ዝም በሉ
እኔም እንድናገር ዕድል ስጡኝ
ከዚያ በኋላ የፈለገው ነገር ይሁን።
14“ጥርሴን ነክሼ ስጨነቅ የምኖረው ለምንድን ነው?
ሕይወቴም በእጄ ላይ ነች።
15ስለዚህ እግዚአብሔር ሊገድለኝ ቢፈልግ
ምንም የሚቀርብኝ ነገር የለም፤
ሆኖም ሁኔታዬን ለእርሱ አስረዳለሁ።
16ኃጢአተኛ ሰው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ ስለማይችል
ምናልባት ይህ ድፍረቴ የመዳን ምክንያት ሊሆን ይችላል።
17እስቲ የምናገረውን ቃል በጥንቃቄ አድምጡ
የማቀርበውንም ማስረጃ ስሙ።
18ክርክሬን በመልካም ሁኔታ አዘጋጅቼ አቅርቤአለሁ፤
እንደሚፈርድልኝም ዐውቃለሁ።
19የሚከሰኝ ካለ፥
ሳልከራከር ጸጥ ብዬ እሞታለሁ።
20ጌታ ሆይ! ከፊትህ እንዳልሰወር
እነዚህን ሁለት ነገሮች አድርግልኝ፤
21ይኸውም የቅጣት ክንድህን ከእኔ ላይ አንሣ፤
አስፈሪ በሆነው ግርማህ አታስደንግጠኝ።
22“አምላክ ሆይ! አንተ በመጀመሪያ ተናገር፤
እኔም መልስ እሰጣለሁ፤
ወይም እኔ ልናገርና አንተ መልስ ስጠኝ።
23ለመሆኑ የሠራሁት በደልና ኃጢአት ምን ያኽል ነው?
እስቲ መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ።
24ፊትህን ከእኔ ሰውረህ እንደ ጠላት
የቈጠርከኝ ስለምንድን ነው?
25ነፋስ እንደሚያረግፈው ቅጠልና እንደ ደረቅ ገለባ
ለምን በማስፈራራት ታሳድደኛለህ?
26“በእኔ ላይ የጻፍከው ክስ እጅግ መራራ ነው፤
በልጅነቴ የሠራሁትን በደል እንኳ አልተውክልኝም፤
27እግሮቼን በግንዶች መካከል አስረሃል፤
እያንዳንዱን እርምጃዬን ትቈጣጠራለህ፤
የእግሬን ዱካ ትመረምራለህ። #ኢዮብ 33፥11። 28ከዚህ የተነሣ እኔ እንደ በሰበሰ ነገር ሆኜ እቀራለሁ፤
ብል እንደ በላውም ልብስ እጠፋለሁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in