ትንቢተ ኢሳይያስ 12
12
የምስጋና መዝሙር
1በዚያን ዘመን እንዲህ ብለህ ትዘምራለህ፦
“ጌታ ሆይ! ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤
አሁን ግን ቊጣህን መልሰህ
ስላጽናናኸኝ አመሰግንሃለሁ።
2በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤
በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤
እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤
እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል። #ዘፀ. 15፥2፤ መዝ. 118፥14።
3ከደኅንነት ምንጭ
ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።”
4በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦
“እግዚአብሔርን አመስግኑ!
ስሙንም አክብሩ!
በሕዝቦች መካከል እርሱ ያደረገውን ተናገሩ!
ስለ ገናናነቱም መስክሩ!
5ስለ ታላቅ ሥራውም ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
ይህም ታላቅ ሥራው በዓለም ሁሉ እንዲታወቅ አድርጉ።
6በእናንተ መካከል ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ስለ ሆነ
በጽዮን የምትኖሩ ሁሉ ‘እልል’ በሉ!”
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 12: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997