መጽሐፈ አስቴር መግቢያ
መግቢያ
በመጽሐፈ አስቴር የተጠቀሱት ድርጊቶች በፋርስ ንጉሠ ነገሥት የክረምት መኖሪያ ስፍራ የተፈጸሙ ሲሆኑ፥ በታላቅ ድፍረቷና ለሕዝቧ ባላት ከፍተኛ ፍቅር፥ ሕዝቧን በጠላቶቻቸው እጅ ከመደምሰስ ባዳነችው፥ አስቴር ተብላ ትጠራ በነበረችው አንዲት አይሁዳዊት ጀግና ሴት ላይ የሚያተኲሩ ናቸው፤ መጽሐፉ “ፑሪም” በመባል ስለሚታወቀው የአይሁድ ክብረ በዓል አጀማመርና ፍች በሚገባ ያስረዳል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የአስቴር ንግሥት መሆን 1፥1—2፥23
ሐማን አይሁድን ለመደምሰስ ማቀዱ 3፥1-15
መርዶክዮስ የአስቴርን ርዳታ መጠየቁ 4፥1-17
መርዶክዮስ ክብር ማግኘቱ 5፥1—6፥14
ሐማን የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት 7፥1-10
አይሁድ ራሳቸውን እንደ ተከላከሉና ጠላቶቻቸውን እንዳጠፉ 8፥1—9፥19
የፑሪም በዓል አከባበር 9፥20-32
የአርጤክስስና የመርዶክዮስ ታላቅነት 10፥1-3
Currently Selected:
መጽሐፈ አስቴር መግቢያ: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997