YouVersion Logo
Search Icon

ትንቢተ ዳንኤል መግቢያ

መግቢያ
ትንቢተ ዳንኤል የተጻፈው አይሁድ በአረማዊ ንጉሥ አገዛዝ ሥር ታላቅ ስደትና ጭቈና ደርሶባቸው በሚሠቃዩበት ወቅት ነበር። ጸሐፊው በታሪኮችና ከራእይ በተገኙ ድርጊቶች መሠረት በጊዜው የነበሩትን ሕዝብ ያጽናናል፤ እግዚአብሔር ጨቋኙን ገዢ አስወግዶ ለሕዝቡ ሉዐላዊነት እንደሚመልስ ተስፋ ይሰጣቸዋል።
መጽሐፉ ሁለት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፦ 1ኛው የዳንኤልና በስደት አብረውት የነበሩት ጥቂት ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ ባላቸው ጽኑ እምነትና ለእርሱም ባላቸው ታዛዥነት ጠላቶቻቸው ስለ ማፈራቸው የሚናገር ታሪክ፥ ይህም ታሪክ የተፈጸመው በባቢሎንና በፋርስ መንግሥታት ዘመን ነው። 2ኛው ደግሞ ዳንኤል ያያቸው ልዩ ልዩ ራእዮች ሲሆኑ፥ እነርሱም ከባቢሎን ጀምሮ ልዩ ልዩ መንግሥታት እየተነሡ እንደሚወድቁና አረማዊው ገዢም ተደምስሶ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ ቀድሞ ቦታው እንደሚመለስ በምሳሌ የታዩ ናቸው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. ዳንኤልና ሦስቱ ጓደኞቹ (1፥1-21)
2. የንጉሥ ናቡከደነፆር ሕልም (2፥1-49)
3. ሲድራቅን፥ ሚሳቅንና አብደናጎን እግዚአብሔር ከሚነድ እሳት ውስጥ እንዳዳናቸው (3፥1-30)
4. ናቡከደነፆር ለሰባት ዓመት መንግሥቱን ማጣቱ (4፥1-37)
5. ንጉሥ ቤልሻጻርና የግድግዳው ላይ ጽሑፍ (5፥1-31)
6. እግዚአብሔር ዳንኤልን ከአንበሳ እንዳዳነው (6፥1-28)
7. ዳንኤል ያየው የአራት አውሬዎች ራእይ (7፥1-28)
8. ዳንኤል ያየው የአውራ በግና የፍየል ራእይ (8፥1-27)
9. ዳንኤል ለሕዝቡ መጸለዩ (9፥1-27)
10. ዳንኤል በጤግሮስ ወንዝ አጠገብ ያየው የእግዚአብሔር መልአክ (10፥1—11፥45)
11. ስለ መጨረሻው ዘመን (12፥1-13)

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in