ወደ ቆላስይስ ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
ይህ መልእክት የተጻፈው በታናሽቱ እስያ ከኤፌሶን በስተ ምሥራቅ በምትገኘው በቆላስይስ ከተማ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ነው፤ ይህች ቤተ ክርስቲያን የተቋቋመችው በጳውሎስ ባይሆንም የሮም ግዛት የሆነችው የእስያ ዋና ከተማ ከሆነችው ከኤፌሶን የወንጌል መልእክተኞችን ያሰማራ ስለ ነበር ለቈላስይስም ኀላፊነት ነበረው፤ በቈላስይስ ቤተ ክርስቲያን “እግዚአብሔርን ለማወቅና የተሟላ መዳንን ለማግኘት እያንዳንዱ ሰው ለመንፈሳዊ ኀይሎችና ሥልጣኖች መስገድ አለበት” የሚሉ ሐሰተኞች መምህራን መኖራቸውን ጳውሎስ ሰምቶ ነበር፤ እነዚህ መምህራን የሚሉት ሌላው ነገር “እያንዳንዱ ሰው እንደ ግዝረት ላሉት ሥርዓቶች መገዛትና የምግብንና የሌሎችንም ደንቦች መጠበቅ አለበት” የሚል ነበር።
ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው እውነተኛውን የክርስትና መልእክት በማቅረብ የእነርሱን ሐሰተኛ ትምህርት ለመቃወም ነበር፤ ካቀረባቸውም መልሶች ዋነኛው “ኢየሱስ ክርስቶስ የተሟላ መዳንን ይሰጣል፤ እነዚህ ሌሎቹ እምነቶችና ተግባሮች ግን ከእርሱ ያርቃሉ” የሚለው ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ፈጠረ፤ በእርሱም በኩል ወደ ራሱ መልሶ ያመጣዋል፤ ዓለም የመዳን ተስፋ የሚኖረው ክርስቶስን ከልብ በማመን ብቻ ነው፤ በዚህ መሠረት ጳውሎስ ይህ ታላቅ ትምህርት በአማኞች ሕይወት እንዴት ሊተረጐም እንደሚችል ያስረዳል።
ይህን መልእክት ከጳውሎስ ተቀብሎ ወደ ቈላስይስ ሊያደርስ ከተላከው ከቲኪቆስ ጋር አብሮ የነበረው አናሲሞስ እንደ ነበረ መመልከት ጠቃሚ ነው፤ ጳውሎስ ስለዚህ ኦኔሲሞስ ስለ ተባለው ባሪያ አንሥቶ ለፊልሞና ሌላ መልእክት ጽፎአል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-8
የክርስቶስ ባሕርይና ሥራ 1፥9—2፥19
በክርስቶስ አዲስ ሕይወት 2፥20—4፥6
ማጠቃለያ 4፥7-18
Currently Selected:
ወደ ቆላስይስ ሰዎች መግቢያ: አማ05
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997