YouVersion Logo
Search Icon

1 የዮሐንስ መልእክት 5

5
ዓለምን ስለ ማሸነፍ
1ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን የሚያምን ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ አባቱን የሚወድ ሁሉ ልጁንም ይወዳል። 2የእግዚአብሔርን ልጆች የምንወድ መሆናችንን የምናውቀው እግዚአብሔርን ስንወድና ትእዛዞቹንም ስንፈጽም ነው። 3እግዚአብሔርንም መውደድ ማለት ትእዛዞቹንም መፈጸም ነው፤ ትእዛዞቹም ከባዶች አይደሉም። #ዮሐ. 14፥15። 4የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል፤ ዓለምን የምናሸንፈውም በእምነታችን ነው። 5ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ከሚያምን ሰው በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማነው?
ስለ ክርስቶስ የተሰጠ ምስክርነት
6ጥምቀቱን በሚያመለክት ውሃና ሞቱን በሚያመለክት ደም የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ የመጣው በውሃ ብቻ ሳይሆን በውሃና በደም ነው። ይህም እውነት ስለ ሆነ ይህ ነገር እውነት መሆኑን መንፈስ ቅዱስ ይመሰክራል፤ 7ሦስት ምስክሮች አሉ፤ 8እነርሱም መንፈስ፥ ውሃና ደም ናቸው፤ እነዚህም ሦስቱ በምስክርነት ይስማማሉ። 9ሰዎች የሚሰጡትን ምስክርነት እንቀበላለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ምስክርነት ከሁሉ ይበልጣል። እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውም ምስክርነት ይህ ነው። 10በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን ይህ ምስክርነት በልቡ ውስጥ አለ፤ እግዚአብሔርን የማያምን ግን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውን ምስክርነት ባለማመኑ ሐሰተኛ አድርጎታል። 11ምስክርነቱም እግዚአብሔር የዘለዓለም ሕይወት እንደ ሰጠንና ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ የሚመሰክር ነው። #ዮሐ. 3፥36። 12የእግዚአብሔር ልጅ ያለው ሕይወት አለው። የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ግን ሕይወት የለውም።
የዘለዓለም ሕይወት
13እናንተ በእግዚአብሔር ልጅ ስም የምታምኑ ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት ያላችሁ መሆኑን እንድታውቁ ይህን ሁሉ ጽፌላችኋለሁ። 14ማንኛውንም ነገር እንደ እርሱ ፈቃድ ብንለምን እንደሚሰማን እንተማመናለን። 15የምንለምነውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን ከእርሱ የምንለምነውን ሁሉ አሁኑኑ እንደምንቀበል እናውቃለን።
16ማንም ሰው ወንድሙ ለሞት የማያደርስ ኃጢአት ሲሠራ ቢያየው ይጸልይለት፤ የሰውዬው ኃጢአት ለሞት የማያደርስ ከሆነ እግዚአብሔር ሕይወትን ይሰጠዋል። ነገር ግን ለሞት የሚያደርስ ኃጢአት አለ። ለእንዲህ ዐይነቱ ኃጢአት ይጸልይ አልልም። 17ክፉ ሥራ ሁሉ ኃጢአት ነው። ይሁን እንጂ ለሞት የማያደርስ ኃጢአት አለ።
18የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሚጠብቀው የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሁሉ ኀጢአት እንደማይሠራ እናውቃለን፤ ሰይጣንም አይነካውም።
19እኛ የእግዚአብሔር መሆናችንን እናውቃለን። ዓለም ግን በሞላው የሰይጣን ተገዢ ሆኖአል።
20የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።
21ልጆች ሆይ! ጣዖቶችን ከማምለክ ራሳችሁን ጠብቁ።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in