YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 148

148
መዝሙር 148
ፍጥረተ ዓለም ሁሉ ያመስግን
1ሃሌ ሉያ።#148፥1 አንዳንዶች ከ14 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።
እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤
በላይ በአርያም አመስግኑት።
2መላእክቱ ሁሉ አመስግኑት፤
ሰራዊቱ ሁሉ አመስግኑት፤
3ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት፤
የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት።
4ሰማየ ሰማያት አመስግኑት፤
ከሰማያትም በላይ ያላችሁ ውሆች አወድሱት።
5እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና፣
የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።
6ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤
የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።
7የባሕር ውስጥ ግዙፍ ፍጥረትና ጥልቅ ውሆች ሁሉ፣
እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት።
8እሳትና በረዶ፣ ዐመዳይና ጭጋግ፣
ትእዛዙንም የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስ፣
9ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፣
የፍሬ ዛፎችና ዝግቦች ሁሉ፣
10የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣
በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበርሩ ወፎችም፣
11የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣
መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣
12ወጣት ወንዶችና ደናግል፣
አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት።
13ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣
ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣
እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ።
14እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን#148፥14 ቀንድ የጥንካሬ ትእምርት ሲሆን፣ ንጉሥን ያመለክታል። አስነሥቷል፤
ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣
እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች።
ሃሌ ሉያ።

Currently Selected:

መዝሙር 148: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in

YouVersion uses cookies to personalize your experience. By using our website, you accept our use of cookies as described in our Privacy Policy