YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 142

142
መዝሙር 142
የሚታደን ሰው ጸሎት
ዋሻ ውስጥ በነበረ ጊዜ፤ የዳዊት ትምህርት፤#142 ርእሱ ላይ ሥነ ጽሑፋዊ ወይም የዜማ ቃል ሊሆን ይችላል። ጸሎት።
1ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤
ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ልመና አቀርባለሁ።
2ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ፤
ችግሬንም በፊቱ እናገራለሁ።
3መንፈሴ በውስጤ ሲዝል፣
መንገዴን የምታውቅ አንተ ነህ፤
በመተላለፊያ መንገዴ ላይ፣
ወጥመድ በስውር ዘርግተውብኛል።
4ወደ ቀኜ ተመልከት፤ እይም፤
ስለ እኔ የሚገድደው የለም፤
ማምለጫም የለኝም፤
ስለ ነፍሴም ደንታ ያለው የለም።
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤
ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤
በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ።
6እጅግ ተስፋ ቈርጫለሁና፣
ጩኸቴን ስማ፤
ከዐቅም በላይ ሆነውብኛልና፣
ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
7ስምህን አመሰግን ዘንድ፣ ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤
ከምታደርግልኝም በጎ ነገር የተነሣ፣
ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።

Currently Selected:

መዝሙር 142: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in