YouVersion Logo
Search Icon

መዝሙር 11

11
መዝሙር 11
የጻድቃን ትምክሕት
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።
1 በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤
ታዲያ ነፍሴን፣ “እንደ ወፍ ወደ ተራራ ብረሪ”
ለምን ትሏታላችሁ?
2ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ?
“ክፉዎች፣ እነሆ፤ ቀስታቸውን ገትረዋል፤
የቅኑን ሰው ልብ በጨለማ ለመንደፍ፣
ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።
3መሠረቱ ከተናደ፣
ጻድቅ ምን ማድረግ ይችላል?”#11፥3 ወይም ጻድቁ ምን እያደረገ ነው?
4 እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤
የእግዚአብሔር ዙፋን በሰማይ ነው።
ዐይኖቹ ሰዎችን ይመለከታሉ፤
ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
5 እግዚአብሔር ጻድቁንና ኀጥኡን ይመረምራል፤#11፥5 ወይም ጻድቁ እግዚአብሔር ኀጥኡን ይመረምራል
ዐመፃን የሚወድዱትን ግን፣
ነፍሱ ትጠላቸዋለች።
6እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤
የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣
የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።
7 እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤
የጽድቅ ሥራም ይወድዳል፤
ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።

Currently Selected:

መዝሙር 11: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in